ነገር ግን፣ “ከእንግዲህ የርሱን ስም አላነሣም፤ በስሙም አልናገርም” ብል፣ ቃሉ በልቤ እንደ እሳት፣ በዐጥንቴም ውስጥ እንደ ረመጥ ሆነብኝ፤ ዐፍኜ መያዝ አቃተኝ፤ ጨርሶ መቋቋም አልቻልሁም።
መዝሙር 39:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልቤ በውስጤ ጋለ፤ በማሰላስልበትም ጊዜ እሳቱ ነደደ፤ ከዚያም በአንደበቴ እንዲህ ተናገርሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዝምታ የተነሣ እንደ ዲዳ ሆንሁ፥ ለበጎ እንኳ ዝም አልሁ፥ ሥቃዬም ተቀሰቀሰብኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልቤ በውስጤ ነደደ፤ በሐሳቤም እሳት ተያያዘ፤ ከዚያም መናገር ጀመርኩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አዲስ ምስጋናን በአፌ ጨመረ፥ ይህም የአምላካችን ምስጋናው ነው፤ ብዙዎች አይተው ይፍሩ፥ በእግዚአብሔርም ይታመኑ። |
ነገር ግን፣ “ከእንግዲህ የርሱን ስም አላነሣም፤ በስሙም አልናገርም” ብል፣ ቃሉ በልቤ እንደ እሳት፣ በዐጥንቴም ውስጥ እንደ ረመጥ ሆነብኝ፤ ዐፍኜ መያዝ አቃተኝ፤ ጨርሶ መቋቋም አልቻልሁም።