ወገቤ እንደ እሳት ነድዷል፤ ሰውነቴም ጤና የለውም።
እጅግ ጐሰቈልሁ ተዋረድሁም፥ ሁልጊዜም በትካዜ እመላለሳለሁ።
ትኲሳት ወገቤን እያቃጠለው ነው፤ ሁለመናዬም ጤና አጣ።
አሁንስ ተስፋዬ ማን ነው? እግዚአብሔር አይደለምን? ትዕግሥቴም ከአንተ ዘንድ ነው።
ለንጉሡም “ንጉሡ ለዘላለም ይኑር፤ አባቶቼ የተቀበሩባት ከተማ ስትፈርስ፣ በሮቿም በእሳት ሲቃጠሉ ለምን ፊቴ አይዘን?” አልሁት።
አምላክ በታላቅ ኀይሉ ልብሴን ጨምድዷል፤ በልብሴም ክሳድ ዐንቆ ይዞኛል።
አካሌ ቈስሎ ትልና ቅርፊት ለብሷል፤ ቈዳዬ አፈክፍኳል፤ ቍስሌም አመርቅዟል።
ዘመኔ እንደ ጢስ ተንኖ ዐልቋልና፤ ዐጥንቶቼም እንደ ማንደጃ ግለዋል።
“ምናምንቴ ነገር ይዞታል፤ ከእንግዲህም ከተኛበት አይነሣም።”
ሄሮድስም ለእግዚአብሔር ክብር ስላልሰጠ የጌታ መልአክ ወዲያው መታው፤ በትልም ተበልቶ ሞተ።