La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መዝሙር 28:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እግዚአብሔር ለሕዝቡ ብርታታቸው ነው፤ ለቀባውም የመዳን ዐምባ ነው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጌታ ለሕዝቡ ኃይላቸው ነው፥ ለቀባውም የመድኃኒቱ መታመኛ ነው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እግዚአብሔር ለሕዝቡ ኀይላቸው ነው፤ ቀብቶ ላነገሠው ንጉሥም የመዳኛ ከለላው ነው።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ምድረ በዳ​ውን ያና​ው​ጣል፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቃ​ዴ​ስን ምድረ በዳ ያና​ው​ጣል።

Ver Capítulo



መዝሙር 28:8
6 Referencias Cruzadas  

ብርቱ አዳኝ የሆንህ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ በጦርነት ዕለት የራስ ቍር ሆንኸኝ።


የምድር ነገሥታት ተነሡ፤ ገዦችም በእግዚአብሔርና በመሲሑ ላይ ሊመክሩ ተሰበሰቡ፤


እግዚአብሔር፣ የቀባውን እንደሚያድን አሁን ዐወቅሁ። የማዳን ኀይል ባለው ቀኝ እጁ፣ ከተቀደሰው ሰማይ ይመልስለታል።


እነዚህ በሠረገላ፣ እነዚያ በፈረስ ይመካሉ፤ እኛ ግን ትምክሕታችን የአምላካችን የእግዚአብሔር ስም ነው።


የጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፤ ለድኾች ወንጌልን እንድሰብክ፣ እግዚአብሔር ቀብቶኛልና። ልባቸው የተሰበረውን እንድጠግን፣ ለምርኮኞች ነጻነትን፣ ለእስረኞች መፈታትን እንዳውጅ ልኮኛል።


ሳሙኤልም የዘይቱን ቀንድ ወስዶ በወንድሞቹ ፊት ቀባው። ከዚያ ቀን ጀምሮ የእግዚአብሔር መንፈስ በዳዊት ላይ በኀይል መጣ፤ ሳሙኤልም ወደ አርማቴም ሄደ።