መዝሙር 140:10 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእሳት ፍም በላያቸው ይውረድ፤ ዳግመኛም እንዳይነሡ ወደ እሳት ይጣሉ፤ ማጥ ወዳለበት ጕድጓድ ይውደቁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሚከብቡኝ ራሳቸውን አነሡ፥ የከንፈራቸው ክፋት ይክደናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእሳት ፍም በላያቸው ይውደቅ፤ ወደ ጒድጓድም ይጣሉ፤ ከዚያም ከቶ አይውጡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ ብቻዬን እስካልፍ ድረስ ኃጥኣን በወጥመዳቸው ይውደቁ። |
በምትገለጥበት ጊዜ፣ እሳት እንደሚንቀለቀልበት ምድጃ ታደርጋቸዋለህ፤ እግዚአብሔር በመዓቱ እንዳልነበሩ ያደርጋቸዋል፤ እሳቱም ሙጥጥ አድርጋ ትበላቸዋለች።
አንተ ግን፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ ክፉዎችን ወደ ጥፋት ጕድጓድ ታወርዳቸዋለህ፤ ደም የተጠሙ ሰዎችና አታላዮች፣ የዘመናቸውን እኩሌታ አይኖሩም። እኔ ግን በአንተ እታመናለሁ።
ነገር ግን ፈሪዎች፣ የማያምኑ፣ ርኩሶች፣ ነፍሰ ገዳዮች፣ አመንዝሮች፣ አስማተኞች፣ ጣዖት አምላኪዎች፣ ውሸተኞች ሁሉ ዕጣ ፈንታቸው በዲንና በእሳት ባሕር ውስጥ መጣል ይሆናል። ይህም ሁለተኛው ሞት ነው።”