መዝሙር 14:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሁሉም ወደ ሌላ ዘወር አሉ፤ በአንድነትም ተበላሹ፤ መልካም የሚያደርግ የለም፤ አንድ እንኳ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሁሉም ዐመፁ በአንድነትም ረከሱ፥ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም፥ አንድም እንኳ የለም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ሁሉም ባዝነዋል፤ ሁሉም በአንድነት ተበላሽተዋል፤ ከእነርሱ አንድ እንኳ መልካም ነገርን የሚያደርግ የለም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአንደበቱ የማይሸነግል፥ በባልንጀራው ላይ ክፋትን የማያደርግ፥ ዘመዶቹንም የማያሰድብ። |
ፈርዖን፣ ሹማምቱና የግብጽ ሕዝብ በሙሉ ሌሊቱን ከመኝታቸው ተነሡ፤ እነሆ በመላዪቱ ግብጽ ልቅሶና ዋይታ ነበር፤ ሰው ያልሞተበት አንድም ቤት አልነበረምና።
ሁላችን እንደ ረከሰ ሰው ሆነናል፤ የጽድቅ ሥራችን እንደ መርገም ጨርቅ ነው፤ ሁላችን እንደ ቅጠል ረግፈናል፤ ኀጢአታችንም እንደ ነፋስ ጠራርጎናል።
“ሕዝቤ ሁለት ኀጢአት ፈጽመዋል፤ ሕያው የውሃ ምንጭ የሆንሁትን፣ እኔን ትተዋል፤ ውሃ መያዝ የማይችሉትን ቀዳዳ የውሃ ማጠራቀሚያ ጕድጓዶች፣ ለራሳቸው ቈፍረዋል።
እንግዲህ፣ ወዳጆች ሆይ፤ ይህ የተስፋ ቃል ስላለን፣ ሥጋንና መንፈስን ከሚያረክስ ነገር ሁሉ ራሳችንን እናንጻ፤ እግዚአብሔርንም በመፍራት ቅድስናችንን ፍጹም እናድርገው።
እኛ ሁላችን በአንድ ወቅት የሥጋችንን ምኞት እያረካን፣ መንገዱንም እየተከተልን በመካከላቸው እንኖር ነበር፤ እንደ ሌሎቹም የቍጣ ልጆች ነበርን።