Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 143:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ሰው ሆኖ በፊትህ ጻድቅ የለምና፣ ባሪያህን ወደ ፍርድ አታቅርበው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ሕያው ሁሉ በፊትህ ጻድቅ አይደለምና ከባርያህ ጋር ወደ ፍርድ አትግባ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 በአንተ ፊት ማንም ጻድቅ ሰው ስለሌለ እኔን አገልጋይህን ለፍርድ አታቅርበኝ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 የሚ​ም​ረኝ፥ መሸ​ሸ​ጊ​ያዬ፥ መጠ​ጊ​ያ​ዬና አዳኜ፤ መታ​መ​ኛ​ዬም፤ እር​ሱን ታመ​ንሁ፤ ሕዝ​ቡ​ንም ከእኔ በታች የሚ​ያ​ስ​ገ​ዛ​ልኝ።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 143:2
12 Referencias Cruzadas  

ትክክለኛውን ነገር የሚያደርግና ፈጽሞ ኀጢአት የማይሠራ ጻድቅ ሰው በምድር ላይ የለም።


ስለዚህ ሕግን በመጠበቅ ማንም ሥጋ ለባሽ በርሱ ፊት ሊጸድቅ አይችልም፤ ይልቁንም በሕግ አማካይነት ኀጢአትን እንገነዘባለን።


ሰው በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ ይሆን ዘንድ፣ ከሴትስ የተወለደ ንጹሕ ይሆን ዘንድ ይችላልን?


ኀጢአት አልሠራንም ብንል፣ እርሱን ሐሰተኛ እናደርገዋለን፤ የእርሱም ቃል በእኛ ውስጥ የለም።


ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን እንጂ፣ ሕግን በመጠበቅ እንደማይጸድቅ እናውቃለን። ስለዚህ ሕግን በመጠበቅ ሳይሆን፣ በክርስቶስ በማመን እንጸድቅ ዘንድ እኛም ደግሞ በክርስቶስ ኢየሱስ አምነናል፤ ሕግን በመጠበቅ ማንም አይጸድቅምና።


እግዚአብሔር ሆይ፤ ኀጢአትን ብትቈጣጠር፣ ጌታ ሆይ፤ ማን ሊቆም ይችላል?


እንደዚህ ባለ ሰው ላይ ዐይንህን ታሳርፋለህን? ለፍርድስ በፊትህ ታቀርበዋለህን?


“ንጹሕ ይሆን ዘንድ ሰው ምንድን ነው? ጻድቅስ ይሆን ዘንድ፣ ከሴት የተወለደ ምንድን ነው?


‘ሥጋ ለባሽ ከእግዚአብሔር ይልቅ ጻድቅ ሊሆን ይችላልን? ሰውስ ከፈጣሪው ይልቅ ንጹሕ ሊሆን ይችላልን?


“መቼም ኀጢአት የማይሠራ ሰው የለምና ሕዝብህ በአንተ ላይ ኀጢአት ቢሠሩ፣ አንተም ተቈጥተህ ለጠላቶቻቸው አሳልፈህ ብትሰጣቸው፣ እነርሱም ሩቅ ወይም ቅርብ ወደ ሆነ የጠላት ምድር ቢጋዙ፣


ፍቅርን ለሺሕዎች የሚጠብቅ፣ ክፋትን፣ ዐመፅንና ኀጢአትን ይቅር የሚል፣ በደለኛውን ግን ሳይቀጣ ዝም ብሎ አይተውም፤ በአባቶች ኀጢአት ልጆችን የልጅ ልጆቻቸውን እስከ ሦስትና አራት ትውልድ ይቀጣል።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios