መዝሙር 135:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ታላቅ እንደ ሆነ፣ ጌታችንም ከአማልክት ሁሉ እንደሚበልጥ ዐውቃለሁና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ታላቅ እንደሆነ፥ ጌታችንም ከአማልክት ሁሉ እንደሚበልጥ አውቄአለሁና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ከአማልክት ሁሉ የሚበልጥ ታላቅ አምላክ መሆኑን ዐውቃለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰማያትን በጥበቡ የሠራ፤ ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፤ |
እርሱ ከምድር ክበብ በላይ በዙፋን ላይ ይቀመጣል፤ ሕዝቦቿም እንደ አንበጣ ናቸው። ሰማያትን እንደ ድባብ ይዘረጋቸዋል፤ እንደ መኖሪያ ድንኳንም ይተክላቸዋል።
ስለዚህ እንደዚህ የሚያድን ሌላ አምላክ የለምና በሲድራቅ፣ በሚሳቅና በአብደናጎ አምላክ ላይ ማንኛውንም ቃል የሚናገሩ ሕዝቦችም ሆኑ ልዩ ልዩ ቋንቋ የሚናገሩ ሁሉ ይቈራረጣሉ፤ ቤቶቻቸውም የፍርስራሽ ክምር ይሆናሉ ብዬ አዝዣለሁ።”
አምላካችሁ እግዚአብሔር የአማልክት አምላክ፣ የጌቶች ጌታ ታላቅ አምላክ፣ ኀያልና የሚያስፈራ፣ አድልዎ የማያደርግ፣ መማለጃም የማይቀበል ነውና።