ድምፁን ባንጐደጐደ ጊዜ በሰማይ ውሆች ይናወጣሉ፤ ጉሙን ከምድር ዳርቻ ወደ ላይ እንዲወጣ ያደርገዋል፤ መብረቅን ከዝናብ ጋራ ይልካል፤ ነፋስንም ከግምጃ ቤቱ ያወጣል።
መዝሙር 135:17 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጆሮ አላቸው፤ አይሰሙም፤ በአፋቸውም እስትንፋስ የለም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጆሮ አላቸው፥ አይሰሙምም፥ እስትንፋስም በአፋቸው የለም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጆሮ አላቸው፤ አይሰሙም፤ በአፍንጫቸውም መተንፈስ አይችሉም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ታላላቅ ነገሥታትን የገደለ፤ ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፤ |
ድምፁን ባንጐደጐደ ጊዜ በሰማይ ውሆች ይናወጣሉ፤ ጉሙን ከምድር ዳርቻ ወደ ላይ እንዲወጣ ያደርገዋል፤ መብረቅን ከዝናብ ጋራ ይልካል፤ ነፋስንም ከግምጃ ቤቱ ያወጣል።
“እያንዳንዳቸው ጅሎችና ዕውቀት የለሽ ናቸው፤ የወርቅ አንጥረኛው ሁሉ በሠራው ጣዖት ዐፍሯል፤ የቀረጻቸው ምስሎቹ የሐሰት ናቸው፤ እስትንፋስም የላቸውም።
አሁንም ኀጢአትን መሥራት አበዙ፤ ብራቸውን አቅልጠው ለራሳቸው ጣዖት ሠሩ፣ በጥበብ የተሠሩ ምስሎችን አበጁ፤ ሁሉም የእጅ ጥበብ ባለሙያ ናቸው። ስለ እነዚህ ሰዎች እንዲህ ተብሏል፤ “ሰውን መሥዋዕት አድርገው ያቀርባሉ፤ የጥጃ ጣዖቶችንም ይስማሉ!”
ዕንጨቱን፣ ‘ንቃ!’ ሕይወት የሌለውንም ድንጋይ፣ ‘ተነሣ!’ ለሚል ወዮለት! በውኑ ማስተማር ይችላልን? እነሆ፤ በወርቅና በብር ተለብጧል፤ እስትንፋስም የለውም።”