መዝሙር 135:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምድራቸውንም ርስት አድርጎ፣ ለሕዝቡ ርስት እንዲሆን ለእስራኤል ሰጠ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምድራቸውንም ርስት አድርጎ ለእስራኤል ለሕዝቡ ርስት ሰጠ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምድራቸውንም ለሕዝቡ ለእስራኤል ርስት አድርጎ ሰጠ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በጸናች እጅ በተዘረጋችም ክንድ፤ ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፤ |
ምድሪቱንም በየጐሣዎቻችሁ በዕጣ ተከፋፈሉ። ከፍ ያለ ቍጥር ላለው ሰፋ ያለውን፣ ዝቅተኛ ቍጥር ላለው ደግሞ አነስተኛውን ስጡ፤ ምንም ይሁን ምን በዕጣ የወጣላቸው፣ የየራሳቸው ርስት ይሆናል። አከፋፈሉም በየአባቶቻችሁ ነገዶች አንጻር ይሁን።
ስለዚህ ኢያሱ እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ምድሪቱን በሙሉ ያዘ፤ እንደ ነገዳቸው አከፋፈል በመመደብም ርስት አድርጎ ለእስራኤላውያን ሰጣቸው። ከዚያም ምድሪቱ ከጦርነት ዐረፈች።
እንግዲህ ኢያሱና እስራኤላውያን ከዮርዳኖስ በስተምዕራብ ድል ያደረጓቸው የምድሪቱ ነገሥታት እነዚህ ናቸው፤ ግዛታቸውም በሊባኖስ ሸለቆ ውስጥ ካለው ከበኣልጋድ ተነሥቶ በምዕራብ ሴይር እስካለው እስከ ሐላቅ ተራራ ይደርሳል፤ ኢያሱም የእነዚህን ነገሥታት ምድር እንደ ነገዳቸው አከፋፈል ለእስራኤላውያን በማከፋፈል ርስት አድርጎ ሰጣቸው።