“አሁን ግን እግዚአብሔር አምላካችን ቅሬታ ይተውልን ዘንድ፣ በመቅደሱም ውስጥ ጽኑ ስፍራ ይሰጠን ዘንድ፣ ለጥቂት ጊዜ ቸርነቱን አሳይቶናል፤ ስለዚህ አምላካችን ለዐይናችን ብርሃን ሰጠን፤ በባርነትም ሳለን ለጥቂት ጊዜ ዕረፍት ሰጠን።
መዝሙር 13:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ ተመልከት፤ ስማኝም። የሞት እንቅልፍ እንዳልተኛ ዐይኖቼን አብራ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እስከ መቼ በነፍሴ እጨነቃለሁ? ትካዜስ እስከ መቼ ዕለቱን በሙሉ በልቤ ይሆናል? እስከ መቼ ጠላቴ በላዬ ይሸልላል? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ! እባክህ አድምጠኝና መልስ ስጠኝ፤ የሞት እንቅልፍ አንቀላፍቼ እንዳልወድቅ ብርታቱን ስጠኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁሉ ተስተካክሎ በአንድነት ዐመፀ፤ በጎ ነገርን የሚሠራት የለም፤ አንድም እንኳ የለም። |
“አሁን ግን እግዚአብሔር አምላካችን ቅሬታ ይተውልን ዘንድ፣ በመቅደሱም ውስጥ ጽኑ ስፍራ ይሰጠን ዘንድ፣ ለጥቂት ጊዜ ቸርነቱን አሳይቶናል፤ ስለዚህ አምላካችን ለዐይናችን ብርሃን ሰጠን፤ በባርነትም ሳለን ለጥቂት ጊዜ ዕረፍት ሰጠን።
ጕረሯቸው በደረቀ ጊዜ ድግስ አዘጋጅላቸዋለሁ፤ እንዲሰክሩም አደርጋቸውና በሣቅ እየፈነደቁ፣ ለዘላለም ላይነቁ ይተኛሉ።” ይላል እግዚአብሔር።
ባለሥልጣኖቿንና ጥበበኞቿን፣ ገዦቿንና መኳንንቷን፣ ጦረኞቿንም አሰክራለሁ፤ ለዘላለም ይተኛሉ፤ አይነቁምም፤” ይላል ስሙ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር የሆነው ንጉሥ።
ምክንያቱም ሁሉን ነገር እንዲታይ የሚያደርገው ብርሃን ነውና፤ ስለዚህም፣ “አንተ የተኛህ ንቃ፤ ከሙታን ተነሣ፤ ክርስቶስም ያበራልሃል” ተብሏል።
ነገር ግን ዮናታን አባቱ ሕዝቡን በመሐላ ማሰሩን አልሰማም ነበር። ስለዚህ በእጁ የያዘውን ዘንግ ጫፍ በማሩ ወለላ ውስጥ በማስገባት እጁን ወደ አፉ አደረገ፤ ዐይኑም በራ።