La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መዝሙር 118:22 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ግንበኞች የናቁት ድንጋይ፣ እርሱ የማእዘን ራስ ሆነ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ግንበኞች የናቁት ድንጋይ፥ እርሱ የማዕዘን ራስ ሆነ፥

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እርሱ ዋና የማእዘን ራስ ሆነ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ትእ​ዛ​ዝ​ህን ፈል​ጌ​አ​ለ​ሁና ስድ​ብ​ንና ነው​ርን ከእኔ አርቅ።

Ver Capítulo



መዝሙር 118:22
8 Referencias Cruzadas  

ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እነሆ፤ የተፈተነ ድንጋይ፣ የመሠረት ድንጋይ፣ ለጽኑ መሠረት የሚሆን የከበረ የማእዘን ድንጋይ፣ በጽዮን አኖራለሁ፤ በርሱም የሚያምን አያፍርም።


“ታላቅ ተራራ ሆይ፤ አንተ ምንድን ነህ? በዘሩባቤል ፊት ደልዳላ ሜዳ ትሆናለህ፤ ሰዎች፣ ‘ሞገስ ይሁንለት! ሞገስ ይሁንለት!’ ብለው እየጮኹ፣ እርሱ መደምደሚያውን ድንጋይ ያወጣል።”


ኢየሱስም፣ “ ‘ግንበኞች የናቁት ድንጋይ፣ የማእዘን ራስ ሆነ፤ ጌታ ይህን አድርጓል፤ ይህም ለዐይናችን ድንቅ ነው።’ ተብሎ በቅዱሳት መጻሕፍት የተጻፈውን አላነበባችሁምን?” አላቸው።


ኢየሱስም ወደ እነርሱ ተመልክቶ እንዲህ አላቸው፤ “ ‘ታዲያ ግንበኞች የናቁት ድንጋይ፣ እርሱ የማእዘን ራስ ሆነ’ ተብሎ የተጻፈው ትርጕሙ ምንድን ነው?


እርሱም፣ “ ‘እናንተ ግንበኞች የናቃችሁት፣ የማእዘን ራስ የሆነው ድንጋይ’ ነው።