መዝሙር 118:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንደ ንብ መንጋ ከበቡኝ፤ ነገር ግን እንደሚነድድ እሾኽ ከሰሙ፤ በርግጥም በእግዚአብሔር ስም አስወግዳቸዋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንብ ማርን እንዲከብብ ከበቡኝ፥ እሳትም በእሾህ ውስጥ እንደሚነድድ ነደዱ፥ በጌታ ስም አጠፋኋቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዙሪያዬን እንደ ንብ ከበቡኝ፤ ነገር ግን እሾኽ በእሳት እንደሚቃጠል በፍጥነት ተቃጠሉ፤ በእግዚአብሔርም ኀይል ደመሰስኳቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ፥ አንተ ቡሩክ ነህ፤ ሥርዐትህንም አስተምረኝ። |
በእነዚያ በተራራማው አገር የሚኖሩት አሞራውያን ሊወጓችሁ ወጡ፤ እንደ ንብ ሰራዊትም ሆነው አባረሯችሁ፤ ከሴይር አንሥቶ እስከ ሖርማ ድረስ አሳድደው መቷችሁ።
ዳዊትም ፍልስጥኤማዊውን እንዲህ አለው፤ “አንተ ሰይፍ፣ ጦርና ጭሬ ይዘህ ትመጣብኛለህ፤ እኔ ግን አንተ በተገዳደርኸው የእስራኤል ሰራዊት ጌታ በሆነው፣ ሁሉን በሚችል በእግዚአብሔር ስም እመጣብሃለሁ።