መዝሙር 106:13 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ያደረገውን ወዲያውኑ ረሱ፤ በምክሩም ለመሄድ አልታገሡም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፈጥነውም ሥራውን ረሱ፥ ምክሩን እንኳን አልጠበቁም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይሁን እንጂ ያደረገላቸውን ድንቅ ነገር ሁሉ ወዲያውኑ ረሱ፤ የእርሱንም ምክር ሳይጠብቁ የራሳቸውን ፈቃድ አደረጉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በተጨነቁ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፥ ከመከራቸውም አዳናቸው። |
እግዚአብሔር ሆይ፤ ማደሪያህ እንዲሆን በሠራኸው ስፍራ፣ ጌታ ሆይ፤ እጆችህ በሠሩት መቅደስ፣ በርስትህ ተራራ ላይ፣ ታመጣቸዋለህ፤ ትተክላቸዋለህም።
ስለዚህ፣ “የምንጠጣውን ውሃ ስጠን” በማለት ሙሴን ተጣሉት። ሙሴም፣ “እኔን ለምን ትጣሉኛላችሁ? እግዚአብሔርንስ ለምን ትፈታተኑታላችሁ?” አለ።
ስፍራውንም ማሳህና መሪባ ብሎ ጠራው፤ እስራኤላውያን ጠብ ፈጥረው፣ “እግዚአብሔር ከእኛ ጋራ ነው ወይስ አይደለም” በማለት እግዚአብሔርን ተፈታትነዋልና።
የፈጠረህን፣ ሰማያትን የዘረጋውን፣ ምድርን የመሠረተውን እግዚአብሔርን ረስተሃል፤ ሊያጠፋህ ከተዘጋጀው፣ ከጨቋኙ ቍጣ የተነሣ፣ በየቀኑ በሽብር ትኖራለህ፤ ታዲያ የጨቋኙ ቍጣ የት አለ?