La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መዝሙር 102:11 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ዘመኖቼ እንደ ምሽት ጥላ ናቸው፤ እኔም እንደ ሣር ደርቄአለሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከቁጣህና ከመዓትህም የተነሣ፥ አንሥተኸኛልና፥ ጥለኸኝማልና።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የሕይወቴ ዘመን እንደ ማታ ጥላ ሆኖአል፤ እንደ ሣርም እጠወልጋለሁ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሰማይ ከም​ድር ከፍ እን​ደ​ሚል፥ እን​ዲሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምሕ​ረ​ቱን በሚ​ፈ​ሩት ላይ አጸና።

Ver Capítulo



መዝሙር 102:11
12 Referencias Cruzadas  

እንደ አበባ ይፈካል፤ ይረግፋልም፤ እንደ ጥላ ይፈጥናል፤ አይጸናምም።


እስክወገድ ድረስ በሁሉ አቅጣጫ አፈራርሶኛል፤ ተስፋዬንም እንደ ዛፍ ነቅሎታል።


እንደ ምሽት ጥላ ከእይታ ተሰውሬአለሁ፤ እንደ አንበጣም ረግፌአለሁ።


ሰው እንደ እስትንፋስ ነው፤ ዘመኑም ፈጥኖ እንደሚያልፍ ጥላ ነው።


ሰው በሕይወት ሳለ፣ እንደ ጥላ በሚያልፉት ጥቂትና ከንቱ በሆኑት ቀኖቹ፣ ለሰው መልካም የሆነውን የሚያውቅ ማን ነው? እርሱ ከሄደ በኋላስ ከፀሓይ በታች የሚሆነውን ማን ሊነግረው ይችላል?


በቍጣው በትር፣ መከራ ያየ ሰው እኔ ነኝ።


ባለጠጋውም ዝቅ በማለቱ ይመካ፤ እንደ ሣር አበባ ይረግፋልና።


ነገ የሚሆነውን እንኳ አታውቁም። ሕይወታችሁ ምንድን ናት? ለጥቂት ጊዜ ታይቶ ኋላ እንደሚጠፋ እንፋሎት ናችሁ።


ምክንያቱም መጽሐፍ እንደሚል፣ “ሥጋ ለባሽ ሁሉ እንደ ሣር ነው፤ ክብሩም ሁሉ እንደ ሜዳ አበባ ነው። ሣሩ ይጠወልጋል፤ አበባውም ይረግፋል፤