ምሳሌ 7:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንዴ በመንገድ፣ አንዴ በአደባባይ፣ በየማእዘኑም ታደባለች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንድ ጊዜ በጎዳና፥ አንድ ጊዜ በአደባባይ፥ በማዕዘኑም ሁሉ ታደባለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በየማእዘኑ፥ በየመንገዱና በየገበያ ስፍራ እየቆመች ትጠባበቃለች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንድ ጊዜ በጎዳና፥ በሌላ ጊዜም በአደባባይ፥ በማዕዘኑም ሁሉ ታደባለች። |
“ከጥንት ጀምሮ ቀንበርሽን ሰበርሁ፤ እስራትሽን በጣጠስሁ፤ አንቺም፣ ‘አላገለግልህም’ አልሽ፤ ከፍ ባለውም ኰረብታ ሁሉ ሥር፣ በእያንዳንዱም ለምለም ዛፍ ሥር፣ ለማመንዘር ተጋደምሽ።
“እስኪ ቀና ብለሽ ጭር ያሉትን ኰረብቶች ተመልከቺ፣ በርኩሰት ያልተጋደምሽበት ቦታ ይገኛልን? በበረሓ እንደ ተቀመጠ ዘላን ዐረብ፣ በየመንገዱ ዳር ተቀምጠሽ ወዳጆችሽን ጠበቅሽ። በዝሙትሽና በክፋትሽ፣ ምድሪቱን አረከስሽ።
በየመንገዱ መጠምዘዣ ላይ ጕብታሽን ባበጀሽና በየአደባባዩም መስገጃ ኰረብታ በሠራሽ ጊዜ እንደ ማንኛውም ዝሙት ዐዳሪ አልነበርሽም፤ ምክንያቱም ዋጋ አላስከፈልሽም።
የመብራት ብርሃን፣ ዳግመኛ በአንቺ ውስጥ አይበራም፤ የሙሽራውና የሙሽራዪቱ ድምፅ፣ ዳግመኛ በአንቺ ውስጥ አይሰማም፤ ነጋዴዎችሽ የዓለም ታላላቅ ሰዎች ነበሩ፤ በአስማትሽም ሕዝቦች ሁሉ ስተዋል።
ሕዝቦች ሁሉ የዝሙቷን ቍጣ ወይን ጠጅ ጠጥተዋልና፤ የምድር ነገሥታት ከርሷ ጋራ አመንዝረዋል፤ የምድርም ነጋዴዎች ከብዙ ምቾቷ ኀይል የተነሣ በልጽገዋል።”