ዳዊትም፣ “ልጄ ሰሎሞን ወጣት ነው፤ ልምዱም የለውም፤ ለእግዚአብሔር የሚሠራው ቤተ መቅደስ ደግሞ እጅግ የሚያምር፣ በአሕዛብም ሁሉ ዘንድ ዝናው የተሰማና እጅግ የተዋበ መሆን አለበት፤ ስለዚህ ሁሉንም እኔ አዘጋጃለሁ” አለ። እንዳለውም ዳዊት ከመሞቱ በፊት በብዛት አዘጋጀ።
ምሳሌ 4:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በአባቴ ቤት ገና ለግላጋ ወጣት፣ ለእናቴም አንድ ልጇ ብቻ በነበርሁ ጊዜ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔም አባቴን የምሰማ ትንሽ ልጅ ነበርሁና፥ በእናቴም ዘንድ እወደድ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔም አንድ ጊዜ ከአባቴ ጋር የምኖር ትንሽ ልጅ ነበርኩ፤ ለእናቴም አንድ ነበርኩ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔም አባቴን የምሰማ ልጅ ነበርሁና፥ በእናቴም ፊት እወደድ ነበር። |
ዳዊትም፣ “ልጄ ሰሎሞን ወጣት ነው፤ ልምዱም የለውም፤ ለእግዚአብሔር የሚሠራው ቤተ መቅደስ ደግሞ እጅግ የሚያምር፣ በአሕዛብም ሁሉ ዘንድ ዝናው የተሰማና እጅግ የተዋበ መሆን አለበት፤ ስለዚህ ሁሉንም እኔ አዘጋጃለሁ” አለ። እንዳለውም ዳዊት ከመሞቱ በፊት በብዛት አዘጋጀ።
ከዚያም ንጉሥ ዳዊት ለመላው ጉባኤ እንዲህ አለ፤ “እግዚአብሔር የመረጠው ልጄ ሰሎሞን ገና ወጣትና ልምድም የሌለው ነው። ይህ ታላቅ ሕንጻ የሚሠራው ለሰው ሳይሆን ለእግዚአብሔር አምላክ በመሆኑ፣ ሥራው ከባድ ነው።
በኢየሩሳሌም የተወለዱለትም ልጆች እነዚህ ነበሩ፤ ሳሙስ፣ ሶባብ፣ ናታን፣ ሰሎሞን፤ እነዚህ አራት ወንዶች ልጆች ከዓሚኤል ልጅ ከቤርሳቤህ የተወለዱ ናቸው።
“በዳዊት ቤትና በኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ላይ የርኅራኄና የልመና መንፈስ አፈስሳለሁ፤ ወደ ወጉኝ ወደ እኔም ይመለከታሉ፤ እነርሱም ለአንድያ ልጅ እንደሚለቀስ ያለቅሱለታል፤ ለበኵር ልጅ ምርር ተብሎ እንደሚለቀስም አምርረው ያለቅሱለታል።”