“አንተም ልጄ ሰሎሞን ሆይ፤ እግዚአብሔር ልብን ሁሉ ስለሚመረምርና ሐሳብን ሁሉ ስለሚያውቅ፣ የአባትህን አምላክ ዕወቅ፤ በፍጹም ልብና በበጎ ፈቃድ አገልግለው። ከፈለግኸው ታገኘዋለህ፤ ከተውኸው ግን እርሱም ለዘላለም ይተውሃል።
ምሳሌ 4:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በጎ ትምህርት እሰጣችኋለሁ፤ ስለዚህ ትምህርቴን አትተዉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መልካም ትምህርትን እሰጣችኋለሁና፥ ሕጌን አትተዉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ የማስተምራችሁ ትምህርት መልካም ስለ ሆነ ቸል አትበሉት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መልካም ስጦታን እሰጣችኋለሁና፥ ሕጌን አትተዉ። |
“አንተም ልጄ ሰሎሞን ሆይ፤ እግዚአብሔር ልብን ሁሉ ስለሚመረምርና ሐሳብን ሁሉ ስለሚያውቅ፣ የአባትህን አምላክ ዕወቅ፤ በፍጹም ልብና በበጎ ፈቃድ አገልግለው። ከፈለግኸው ታገኘዋለህ፤ ከተውኸው ግን እርሱም ለዘላለም ይተውሃል።
“እናንተ ግን እኔን ከመከተል ተመልሳችሁ የሰጠኋችሁን ሥርዐቶቼንና ትእዛዞቼን ብትተዉ፣ ሄዳችሁም ሌሎችን አማልክት ብታገለግሉና ብታመልኳቸው፣
እኛም አባታችን የሬካብ ልጅ ኢዮናዳብ ያዘዘንን ሁሉ ፈጽመናል፤ እኛና ሚስቶቻችን፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችንም የወይን ጠጅ ጠጥተን አናውቅም፤
ትምህርቴ እንደ ዝናብ ትውረድ፤ ቃሌም እንደ ጤዛ ይንጠባጠብ፤ በቡቃያ ሣር ላይ እንደ ካፊያ፣ ለጋ ተክልም ላይ እንደ ከባድ ዝናብ ይውረድ።
ሌሎችን ትክክል በሆነው ትምህርት እንዲያበረታታና ይህንኑ ትምህርት የሚቃወሙትን ይወቅሥ ዘንድ እንደ ተማረው በታመነ ቃል የሚጸና መሆን አለበት።