ምሳሌ 21:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለሰው መንገዱ ሁሉ ቀና ይመስለዋል፤ እግዚአብሔር ግን ልብን ይመዝናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሰው መንገድ ሁሉ በዓይኑ ፊት የቀናች ትመስለዋለች፥ ጌታ ግን ልብን ይመዝናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰው የሚያደርገው ነገር ሁሉ ትክክል ይመስለዋል፤ እግዚአብሔር ግን የልብን ሐሳብ ይመዝናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰው ሁሉ ለራሱ ጻድቅ መስሎ ይታያል፤ እግዚአብሔር ግን ልብን ያቀናል። |
አንተም፣ “ስለዚህ ነገር ምንም አላውቅም” ብትል፣ ልብን የሚመረምር እርሱ አያስተውልምን? ሕይወትህን የሚጠብቃት እርሱ አያውቅምን? ለእያንዳንዱ ሰው እንደ ሥራው መጠን አይከፍለውምን?
እርሱም እንዲህ አላቸው፤ “እናንተ በሰዎች ፊት ራሳችሁን የምታጸድቁ ናችሁ፤ እግዚአብሔር ግን ልባችሁን ያውቃል፤ በሰዎች ዘንድ የከበረ፣ በእግዚአብሔር ፊት የረከሰ ነውና።
ልጆቿንም በሞት እቀጣቸዋለሁ። ከዚያም አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ እኔ ልብንና ሐሳብን የምመረምር መሆኔን ይረዳሉ፤ ለእያንዳንዳችሁም እንደ ሥራችሁ እከፍላችኋለሁ።
እግዚአብሔር ግን ሳሙኤልን፣ “መልኩን ወይም ቁመቱን አትይ፤ እኔ ንቄዋለሁና። እግዚአብሔር የሚያየው፣ ሰው እንደሚያየው አይደለም። ሰው የውጭውን ገጽታ ያያል፤ እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል” አለው።