ምሳሌ 13:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጻድቅ ሐሰትን ይጠላል፤ ክፉ ሰው ግን ኀፍረትንና ውርደትን ያመጣል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጻድቅ ሐሰትን ይጠላል፥ ኀጥእ ግን ያሳፍራል ያስነውራልም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደጋግ ሰዎች ሐሰትን ይጠላሉ፤ የክፉዎች ሰዎች ንግግር ግን አሳፋሪና አስነዋሪ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጻድቅ የሐሰትን ቃል ይጠላል፤ ኀጢአተኛ ግን ያፍራል፥ ተገልጦም አይመጣም። |
እነዚህ ከሰይፍ የተረፉት፣ ከእኔ ዘወር ባለ አመንዝራ ልባቸውና ጣዖትን በተከተለ አመንዝራ ዐይናቸው የቱን ያህል እንዳሳዘኑኝ፤ በአሕዛብ ምድር ሆነው ያስታውሱኛል፤ ካደረጉት ክፋትና ከፈጸሙት ርኩስ ተግባር ሁሉ የተነሣም ራሳቸውን ይጸየፋሉ።
ነገር ግን ፈሪዎች፣ የማያምኑ፣ ርኩሶች፣ ነፍሰ ገዳዮች፣ አመንዝሮች፣ አስማተኞች፣ ጣዖት አምላኪዎች፣ ውሸተኞች ሁሉ ዕጣ ፈንታቸው በዲንና በእሳት ባሕር ውስጥ መጣል ይሆናል። ይህም ሁለተኛው ሞት ነው።”