ምሳሌ 12:1 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ተግሣጽን የሚወድድ ዕውቀትን ይወድዳል፤ መታረምን የሚጠላ ግን ደነዝ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ተግሣጽን የሚወድድ እውቀትን ይወድዳል፥ እርማትን የሚጠላ ግን ሞኝ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዕውቀትን የሚወድ ሰው ከስሕተት መታረምን ይወዳል፤ ተግሣጽን የሚጠላ ግን ጅል ሰው ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ተግሣጽን የሚወድድ ዕውቀትን ይወድዳል፤ ተግሣጽን የሚጠላ ግን ሰነፍ ነው። |
ጻድቅ ሰው ይቅጣኝ፤ ይህ በጎነት ነው፤ ይገሥጸኝም፤ በራሴ ላይ እንደሚፈስስ ዘይት ነው፤ ራሴም ይህን እንቢ አይልም። ጸሎቴ ግን በክፉዎች ተግባር ላይ ነው።