Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ምሳሌ 10:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 በልቡ ጠቢብ የሆነ ትእዛዝ ይቀበላል፤ ለፍላፊ ቂል ግን ወደ ጥፋት ያመራል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 በልቡ ጠቢብ የሆነ ትእዛዝን ይቀበላል፥ በከንፈሩ ሞኝ የሆነ ግን ይወድቃል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 በእውነት ጥበበኛ የሆነ ሰው ትእዝዞችን ይቀበላል፤ የሚለፈልፉ ሞኞች ግን ወደ ጥፋት ያመራሉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 በልቡ ጠቢብ የሆነ ትእዛዝን ይቀበላል፤ በከንፈሩ የማይታገሥ ግን በመሰናክል ይወድቃል።

Ver Capítulo Copiar




ምሳሌ 10:8
15 Referencias Cruzadas  

ሕግህን እንድጠብቅ፣ በፍጹም ልቤም እንድታዘዘው፣ ማስተዋልን ስጠኝ።


ጥበበኞች ያድምጡ፤ ትምህርታቸውንም ያዳብሩ፤ አስተዋዮችም መመሪያ ያግኙበት፤


በተንኰለኛ ዐይን የሚጠቅስ ሐዘን ያስከትላል፤ ለፍላፊ ቂልም ወደ ጥፋት ያመራል።


ጠቢባን ዕውቀት ያከማቻሉ፤ የቂል አንደበት ግን ጥፋትን ይጋብዛል።


ተግሣጽን የሚወድድ ዕውቀትን ይወድዳል፤ መታረምን የሚጠላ ግን ደነዝ ነው።


ክፉ ሰው በክፉ ንግግሩ ይጠመዳል፤ ጻድቅ ሰው ግን ከመከራ ያመልጣል።


አንደበቱን የሚጠብቅ ሕይወቱን ይጠብቃል፤ አፉ እንዳመጣለት የሚናገር ግን ይጠፋል።


ለፍተው የሠሩት ሁሉ ትርፍ ያስገኛል፤ ከንቱ ወሬ ግን ወደ ድኽነት ያመራል።


የአስተዋዮች ጥበብ መንገዳቸውን ልብ ማለት ነው፤ የሞኞች ቂልነት ግን መታለል ነው።


ፌዘኛን አትዝለፈው፤ ይጠላሃል፤ ጠቢብን ገሥጸው፤ ይወድድሃል።


ጠቢብን አስተምረው፣ ይበልጥ ጥበበኛ ይሆናል፤ ጻድቁን ሰው አስተምረው፤ ዕውቀቱን ይጨምራል።


ከጠቢብ አፍ የሚወጣ ቃል ባለሞገስ ነው፤ ሞኝ ግን በገዛ ከንፈሩ ይጠፋል፤


ከእናንተ መካከል ጥበበኛና አስተዋይ የሆነ ሰው ማን ነው? ሥራውን ከጥበብ በሆነ በመልካም አኗኗር ያሳይ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos