አኪጦፌልም ምክሩን እንዳልተከተሉት ባየ ጊዜ፣ አህያውን ጭኖ ቤቱ ወደሚገኝበት ወደ መኖሪያ ከተማው ሄደ፤ ቤቱንም መልክ መልክ ካስያዘ በኋላ በገዛ እጁ ታንቆ ሞተ። በዚህ ሁኔታም ሞቶ በአባቱ መቃብር ተቀበረ።
ምሳሌ 11:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለፍጹማን ሰዎች ጽድቃቸው መንገዳቸውን ታቃናላቸዋለች፤ ክፉዎች ግን በገዛ ክፋታቸው ይወድቃሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የፍጹም ሰው ጽድቁ መንገዱን ያቀናለታል፥ ክፉ ግን በክፋቱ ይወድቃል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደግነት የመልካሙን ሰው ኑሮ ያቃናለታል፤ ክፉ ሰው ግን በገዛ ክፋቱ ይወድቃል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የፍጹም ሰው ጽድቁ መንገዱን ያቀናለታል፤ ኀጢአት ግን በክፉዎች ላይ ትወርዳለች። |
አኪጦፌልም ምክሩን እንዳልተከተሉት ባየ ጊዜ፣ አህያውን ጭኖ ቤቱ ወደሚገኝበት ወደ መኖሪያ ከተማው ሄደ፤ ቤቱንም መልክ መልክ ካስያዘ በኋላ በገዛ እጁ ታንቆ ሞተ። በዚህ ሁኔታም ሞቶ በአባቱ መቃብር ተቀበረ።