ምሳሌ 1:18 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነዚህ ሰዎች የሚያደቡት በገዛ ደማቸው ላይ ነው፤ የሚሸምቁትም በራሳቸው ላይ ብቻ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም በደማቸው ላይ ያደባሉ፥ በነፍሳቸውም ላይ ይሸምቃሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህን የሚያደርጉ ሰዎች የሚሞቱበትን ወጥመድ ራሳቸው ይዘረጋሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መግደልን የለመዱ እነርሱ ክፋትን ለራሳቸው ይሰበስባሉ። የኀጢአተኞች ሰዎች አወዳደቃቸው ክፉ ነው። |
አንተ ግን፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ ክፉዎችን ወደ ጥፋት ጕድጓድ ታወርዳቸዋለህ፤ ደም የተጠሙ ሰዎችና አታላዮች፣ የዘመናቸውን እኩሌታ አይኖሩም። እኔ ግን በአንተ እታመናለሁ።