ፊልጵስዩስ 1:1 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የክርስቶስ ኢየሱስ ባሮች የሆኑ ጳውሎስና ጢሞቴዎስ፤ ከቤተ ክርስቲያን ኤጲስ ቆጶሳትና ከዲያቆናት ጋራ በፊልጵስዩስ ላሉ በክርስቶስ ኢየሱስ ቅዱሳን ለሆኑ ሁሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የኢየሱስ ክርስቶስ ባርያዎች የሆኑ ጳውሎስና ጢሞቴዎስ፥ በፊልጵስዩስ ለሚኖሩ ከኤጲስ ቆጶሳትና ከዲያቆናት ጋር በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት ቅዱሳን ሁሉ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋዮች ከሆኑት ከጳውሎስና ከጢሞቴዎስ፥ በፊልጵስዩስ ከተማ ለሚኖሩ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱሳን ለሆኑ ሁሉ፥ እንዲሁም ለኤጲስ ቆጶሳትና ዲያቆናት፦ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከኢየሱስ ክርስቶስ ባርያዎች ከጳውሎስና ከጢሞቴዎስ፥ በፊልጵስዩስ ለሚኖሩ፤ ከቀሳውስትና ከዲያቆናት ጋር በኢየሱስ ክርስቶስ ላሉ ቅዱሳን ሁሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያዎች የሆኑ ጳውሎስና ጢሞቴዎስ በፊልጵስዩስ ለሚኖሩ ከኤጲስ ቆጶሳትና ከዲያቆናት ጋር በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት ቅዱሳን ሁሉ፦ |
ጴጥሮስም በመቀጠል እንዲህ አለ፤ “በመዝሙር መጽሐፍ፣ ‘መኖሪያው ባድማ ትሁን፤ የሚኖርባትም አይገኝ’ ደግሞም፣ ‘ሹመቱንም ሌላ ይውሰደው’ ተብሎ ተጽፏል።
ለራሳችሁና መንፈስ ቅዱስ ኤጲስ ቆጶሳት አድርጎ በላዩ ለሾማችሁ መንጋ ሁሉ ተጠንቀቁ፤ በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ጠብቁ።
ሐናንያም መልሶ እንዲህ አለው፤ “ጌታ ሆይ፤ ይህ ሰው እኮ በኢየሩሳሌም ባሉ ቅዱሳንህ ላይ ምን ያህል ጕዳት እንዳደረሰ ከብዙ ሰው ሰምቻለሁ፤
በእግዚአብሔር ለተወደዳችሁና ቅዱሳን ለመሆን ለተጠራችሁ በሮም ላላችሁ ሁሉ፤ ከአባታችን ከእግዚአብሔር፣ ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።
በእግዚአብሔር ፈቃድ የክርስቶስ ኢየሱስ ሐዋርያ ከሆነው ከጳውሎስ፣ ከወንድማችንም ከጢሞቴዎስ፤ በቆሮንቶስ ላለችው ለእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን እንዲሁም በመላው አካይያ ለሚኖሩ ቅዱሳን ሁሉ፤
አሁን እኔ ተቀባይነት ለማግኘት የምሻው በሰዎች ዘንድ ነው ወይስ በእግዚአብሔር ዘንድ? ወይስ ሰዎችን ደስ ለማሠኘት እየተጣጣርሁ ነው? ሰዎችን ደስ ለማሠኘት የምጥር ብሆን ኖሮ፣ የክርስቶስ ባሪያ ባልሆንሁ ነበር።
ይህን ሁሉ አግኝቻለሁ ወይም ፍጹም ሆኛለሁ ማለት አይደለም፤ ነገር ግን ክርስቶስ ኢየሱስ እኔን የራሱ ያደረገበትን ያን፣ እኔም የራሴ ለማድረግ እጣጣራለሁ።
ከዚህም በላይ ለርሱ ብዬ ሁሉን ነገር የተውሁለትን፣ ወደር የሌለውን ጌታዬን ክርስቶስ ኢየሱስን ከማወቅ ታላቅነት ጋራ ሳነጻጽር፣ ሁሉንም ነገር እንደ ጕድለት እቈጥረዋለሁ፤ ለርሱ ስል ሁሉን ዐጥቻለሁ፤ ክርስቶስን አገኝ ዘንድ ሁሉን እንደ ጕድፍ እቈጥራለሁ፤
ከጳውሎስ፣ ከሲላስና ከጢሞቴዎስ፤ በእግዚአብሔር አብና በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ለሆኑት ለተሰሎንቄ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን፤ ከእግዚአብሔር አብ ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።
እንደምታውቁት ከዚህ ቀደም በፊልጵስዩስ መከራ ተቀብለን ተንገላታን፤ ነገር ግን ብርቱ ተቃውሞ ቢደርስብንም እንኳ፣ የእግዚአብሔርን ወንጌል ለእናንተ እንደምናበሥር በአምላካችን ድፍረት አገኘን።
የሚቀጡትም በቅዱሳኑ ዘንድ ሊከብርና በሚያምኑበትም ሁሉ ሊገረም በሚመጣበት በዚያ ቀን ይሆናል፤ እናንተም ከሚያምኑት መካከል ናችሁ፤ ምስክርነታችንን ተቀብላችኋልና።
ዲያቆናትም እንደዚሁ የተከበሩ፣ ቃላቸውን የማይለዋውጡ፣ ለብዙ ወይን ጠጅ የማይጐመጁ፣ ያለ አግባብ የሚገኝ ጥቅምንም የማያሳድዱ ሰዎች መሆን ይገባቸዋል፤
የእግዚአብሔርን ምርጦች እምነትና ወደ እውነተኛ መንፈሳዊነት የሚመራውን የእውነት ዕውቀት ለማሳደግ የእግዚአብሔር ባሪያና የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ የሆነው ጳውሎስ፤
ኤጲስ ቆጶስ የእግዚአብሔር ሥራ ባለዐደራ እንደ መሆኑ የማይነቀፍ ሊሆን ይገባል፤ ይኸውም ትምክሕተኛ፣ ግልፍተኛ፣ ሰካራም፣ ጨቅጫቃና ተገቢ ባልሆነ መንገድ ለጥቅም የሚሮጥ ሊሆን አይገባም።
የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያና ሐዋርያ ስምዖን ጴጥሮስ፤ በአምላካችንና በአዳኛችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጽድቅ በኩል እንደ ተቀበልነው ዐይነት ክቡር እምነት ለተቀበሉት፤
ቶሎ መሆን የሚገባውን ነገር ለባሮቹ እንዲያሳይ፣ እግዚአብሔር ለርሱ የሰጠው የኢየሱስ ክርስቶስ ራእይ ይህ ነው፤ ኢየሱስም መልአኩን ልኮ ለባሪያው ለዮሐንስ ገለጠለት፤
በቀኝ እጄ ያየሃቸው የሰባቱ ከዋክብትና የሰባቱ የወርቅ መቅረዞች ምስጢር ይህ ነው፤ ሰባቱ ከዋክብት የሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት መላእክት ናቸው፤ ሰባቱ መቅረዞች ደግሞ ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ናቸው።
እኔም ልሰግድለት በእግሩ ሥር ተደፋሁ፤ እርሱ ግን፣ “ተው! ይህን አታድርግ! እኔም ከአንተና የኢየሱስን ምስክር ከያዙት ወንድሞችህ ጋራ አገልጋይ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ፤ የኢየሱስ ምስክር የትንቢት መንፈስ ነውና” አለኝ።
እርሱ ግን፣ “ተው፤ ይህን አታድርግ እኔ ከአንተና ከወንድሞችህ ከነቢያት እንዲሁም የዚህን መጽሐፍ ቃል ከሚጠብቁት ሁሉ ጋራ አገልጋይ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ” አለኝ።