ዘኍል 9:17 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደመናው ከድንኳኑ ላይ በሚነሣበት ጊዜ እስራኤላውያን ጕዟቸውን ይጀምሩ ነበር፤ ደመናው በሚቆምበት ቦታ ደግሞ ይሰፍሩ ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደመናውም ከድንኳኑ ላይ በማናቸውም ጊዜ ሲነሣ በዚያን ጊዜ የእስራኤል ልጆች ይጓዙ ነበር፤ ደመናውም ባረፈበት ስፍራ በዚያ የእስራኤል ልጆች ይሰፍሩ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደመናው ከድንኳኑ ላይ በሚነሣበት ጊዜ ሁሉ እስራኤላውያን ሰፈራቸውን ለቀው ይጓዙ ነበር፤ ደመናውም በሚወርድበት ቦታ እንደገና ይሰፍሩ ነበር፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደመናውም ከድንኳኑ ላይ በተነሣ ጊዜ በዚያን ጊዜ የእስራኤል ልጆች ይጓዙ ነበር፤ ደመናውም በቆመበት ስፍራ በዚያ የእስራኤል ልጆች ይሰፍሩ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደመናውም ከድንኳኑ ላይ በተነሣ ጊዜ በዚያን ጊዜ የእስራኤል ልጆች ይጓዙ ነበር፤ ደመናውም በቆመበት ስፍራ በዚያ የእስራኤል ልጆች ይሰፍሩ ነበር። |
መላው የእስራኤል ማኅበር ከሲና ምድረ በዳ ተነሥቶ እግዚአብሔር እንዳዘዘው ከስፍራ ወደ ስፍራ ተጕዞ በራፊዲም ሰፈረ፤ ነገር ግን ሕዝቡ የሚጠጡት ውሃ አልነበረም።