ዘኍል 4:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ደግሞም ሰማያዊ ጨርቅ ወስደው ማብሪያ መቅረዙንና መብራቶቹን፣ መኰስተሪያዎቹንና የኵስታሪ መቀበያዎቹን፣ እንዲሁም ለዚሁ አገልግሎት የሚውሉትን የዘይት ዕቃዎች ይሸፍኑበት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰማያዊውንም መጐናጸፊያ ይውሰዱ፥ የመብራቱንም መቅረዝ፥ ቀንዲሎቹንም፥ መቆንጠጫዎቹንም፥ መተርኮሻዎቹንም፥ ዘይቱንም የሚያቀርቡባቸውን ዕቃዎች ሁሉ ይሸፍኑ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ሰማያዊ ጨርቅ ወስደው መቅረዙን፥ ከነመብራቶቹ ከመኮስተሪያዎቹና ከኩስታሪ ማኖሪያዎቹ፥ እንዲሁም ከዘይት ዕቃዎቹ ሁሉ ጋር ይሸፍኑት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰማያዊውንም መጐናጸፊያ ይውሰዱ፤ የሚያበሩባትንም መቅረዝ፥ ቀንዲሎችዋንም፥ መኰስተሪያዎችዋንም፥ የኵስታሪ ማድረጊያዎችዋንም፥ እርስዋንም ለማገልገል የዘይቱን ማሰሮዎች ሁሉ ይሸፍኑ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰማያዊውንም መጐናጸፊያ ይውሰዱ፥ የሚያበራውንም መቅረዝ፥ ቀንዲሎቹንም፥ መኰስተሪያዎቹንም፥ የኩስታሪ ማድረጊያዎቹንም፥ እርሱንም ለማገልገል የዘይቱን ዕቃዎች ሁሉ ይሸፍኑ፤ |
በቀኝ እጄ ያየሃቸው የሰባቱ ከዋክብትና የሰባቱ የወርቅ መቅረዞች ምስጢር ይህ ነው፤ ሰባቱ ከዋክብት የሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት መላእክት ናቸው፤ ሰባቱ መቅረዞች ደግሞ ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ናቸው።