ዘኍል 34:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስከ ዚፍሮን በመቀጠል መጨረሻው ሐጻርዔናን ይሆናል፤ በሰሜን በኩል ያለው ወሰናችሁ ይኸው ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ድንበሩም ወደ ዚፍሮን ይዘረጋል መጨረሻውም ሐጸርዔናን ይሆናል፤ ይህ የሰሜን ድንበራችሁ ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ ዚፍሮን ከተሻገረም በኋላ በሐጻርዔናን ይቆማል፤ ይህም የሰሜን ድንበራችሁ ይሆናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳርቻውም ወደ ዲፍሮና ያልፋል፤ መውጫውም አርሴናይን ይሆናል፤ በመስዕ በኩል ያለው ወሰናችሁም በዚህ ይሁናችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳርቻውም ወደ ዚፍሮን ያልፋል እስከ ሐጸርዔናንም ድረስ ይወጣል፤ ይህ የሰሜን ዳርቻችሁ ይሆናል። |
“ስማቸው የተዘረዘረው ነገዶች እነዚህ ናቸው፤ “በሰሜኑ ድንበር የዳን ነገድ አንድ ድርሻ ይኖረዋል፤ ይህም የሔትሎንን መንገድ ተከትሎ እስከ ሐማት መተላለፊያ ይደርሳል። ሐጻርዔናንና ከሐማት ቀጥሎ ያለው የደማስቆ ሰሜናዊ ድንበር ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ላለው ወሰኑ አንድ ክፍል ይሆናል።