ዘኍል 32:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርን በፍጹም ልባቸው ተከትለውታልና፣ ከቄኔዛዊው ከዮፎኒ ልጅ ከካሌብና ከነዌ ልጅ ከኢያሱ በቀር አንዳቸውም አያዩዋትም።’ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳሩ ግን ለዮፎኔ ልጅ ካሌብና ለነዌ ልጅ ለኢያሱ በእውነት ጌታን ፈጽመው ስለ ተከተሉ ይህ እንዲህ አይሆንም።’ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም የእግዚአብሔር ውሳኔ እግዚአብሔርን በሙሉ ልባቸው ከታዘዙት ከቀኒዛዊው ከየፉኔ ልጅ ከካሌብና ከነዌ ልጅ ከኢያሱ በቀር ማንኛውንም ሰው የሚያጠቃልል ነው። ለእግዚአብሔር ታማኞች ሆነው የተገኙት እነርሱ ብቻ ናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርን ተከትለዋልና ከእነዚህ፥ ልዩ ከሆነ ከዮፎኒ ልጅ ከካሌብና ከነዌ ልጅ ከኢያሱ በቀር፤ |
አገልጋዬ ካሌብ ግን የተለየ መንፈስ ስላለውና በፍጹም ልቡ የተከተለኝ በመሆኑ ሄዶባት ወደ ነበረችው ምድር አስገባዋለሁ፤ ዘሮቹም ይወርሷታል።
ምክንያቱም በርግጥ በምድረ በዳ እንደሚሞቱ ያን ጊዜ እግዚአብሔር ነግሯቸው ነበር፤ ከዮፎኒ ልጅ ከካሌብና ከነዌ ልጅ ከኢያሱ በቀር ከእነርሱ የተረፈ ማንም ሰው አልነበረም።
ከዮፎኒ ልጅ ከካሌብ በቀር የሚያያት የለም፤ እርሱ ያያታል፤ እግዚአብሔርን በፍጹም ልቡ ስለ ተከተለ፣ የረገጣትን ምድር ለርሱና ለዘሮቹ እሰጣለሁ።”