ዘኍል 26:61 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ናዳብና አብዩድ ባልተፈቀደ እሳት ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ስላቀረቡ ሞቱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጌታም ፊት ያልተፈቀደውን እሳት ባቀረቡ ጊዜ ናዳብና አብዩድ ሞቱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ናዳብና አቢሁ ያልተቀደሰ እሳት ለእግዚአብሔር ከማቅረባቸው የተነሣ ተቀሥፈው ሞቱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሲና በረሃ በእግዚአብሔር ፊት ከሌላ እሳት ባቀረቡ ጊዜ ናዳብና አብዩድ ሞቱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእግዚአብሔርም ፊት ሌላ እሳት ባቀረቡ ጊዜ ናዳብና አብዩድ ሞቱ። |
ናዳብና አብዩድ ግን በሲና ምድረ በዳ ባልተፈቀደ እሳት ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ባቀረቡ ጊዜ እዚያው እፊቱ ወድቀው ሞቱ። ወንዶች ልጆች ስላልነበሯቸውም አልዓዛርና ኢታምር ብቻ አባታቸው አሮን በሕይወት በነበረበት ዘመን በክህነት ያገለግሉ ነበር።