የምድያም ነጋዴዎችም እነርሱ ዘንድ እንደ ደረሱ፣ ወንድሞቹ ዮሴፍን ከጕድጓድ አውጥተው ለእስማኤላውያን በሃያ ጥሬ ብር ሸጡላቸው፤ እነርሱም ዮሴፍን ወደ ግብጽ ወሰዱት።
ዘኍል 25:14 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከምድያማዊቷ ሴት ጋራ የተገደለው እስራኤላዊ የሰሉ ልጅ ዘንበሪ ይባላል፤ የስምዖናውያን ቤተ ሰብ አለቃ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከምድያማዊቱም ጋር የተገደለው የእስራኤላዊው ሰው ስም ዘንበሪ ይባል ነበረ፤ እርሱም የስምዖናውያን ወገን የአባቱ ቤት አለቃ የሆነ የሰሉ ልጅ ነበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከምድያማዊቱ ሴት ጋር የተገደለው እስራኤላዊ ስም የሳሉ ልጅ ዚምሪ ሲሆን እርሱም በስምዖን ነገድ ውስጥ የጐሣ አለቃ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከምድያማዊቱም ጋር የተገደለው የእስራኤላዊው ሰው ስም ዘንበሪ ነበረ፤ የአባቱ ቤት አለቃ የስምዖናውያን የሆነ የሰሉ ልጅ ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከምድያማዊቱም ጋር የተገደለው የእስራኤላዊው ሰው ስም ዘንበሪ ነበረ፤ የአባቱ ቤት አለቃ የስምዖናውያን የሆነ የሰሉ ልጅ ነበረ። |
የምድያም ነጋዴዎችም እነርሱ ዘንድ እንደ ደረሱ፣ ወንድሞቹ ዮሴፍን ከጕድጓድ አውጥተው ለእስማኤላውያን በሃያ ጥሬ ብር ሸጡላቸው፤ እነርሱም ዮሴፍን ወደ ግብጽ ወሰዱት።
እነርሱም ከምድያም ተነሥተው ወደ ፋራን ሄዱ፤ ከፋራንም ሰዎች ይዘው ወደ ግብጽ በመምጣት፣ ወደ ግብጽ ንጉሥ ወደ ፈርዖን ገቡ። ንጉሡም ለሃዳድ ቤትና መሬት ሰጠው፤ ቀለብም አዘዘለት።
የየነገዱ የእስራኤል የጦር ሹማምት፤ በሮቤል ነገድ ላይ የተሾመው፣ የዝክሪ ልጅ አልዓዛር፤ በስምዖን ነገድ ላይ የተሾመው፣ የመዓካ ልጅ ሰፋጥያስ።
አሁንም እግዚአብሔርን መፍራት በእናንተ ላይ ይሁን፤ በአምላካችን በእግዚአብሔር ዘንድ ፍርድ ማጣመም፣ አድልዎ ማድረግና መማለጃ መቀበል ስለሌለ ተጠንቅቃችሁ ፍረዱ።”