ዘኍል 24:22 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያም ሆኖ ግን እናንተ ቄናውያን፤ አሦር በምርኮ ሲወስዳችሁ ትደመሰሳላችሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቄናዊው ግን ለጥፋት የተዘጋጀ ይሆናል። አሦር የሚማርክህ እስከ መቼ ድረስ ይሆን?” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ ቄናውያን፥ አሦር ድል ነሥታ በምትማርካችሁ ጊዜ ትደመሰሳላችሁ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቢዖር የጥፋት ጎጆ ቢሆንም አሦር ይማርክሃል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን አሦር እስኪማርክህ ድረስ ቄናዊው ለጥፋት ይሆናል። |
ወደ ዘሩባቤልና ወደ ቤተ ሰቡ አለቆች መጥተው፣ “እኛም እንደ እናንተ አምላካችሁን የምንፈልግ ነን፤ የአሦር ንጉሥ አስራዶን ወደዚህ ካመጣን ጊዜ ጀምሮ ለርሱ ስንሠዋለት ቈይተናል፤ ስለዚህ ዐብረን ከእናንተ ጋራ እንሥራ” አሏቸው።
አሦር ሊያድነን አይችልም፤ በጦር ፈረሶችም ላይ አንቀመጥም፤ ከእንግዲህም የገዛ እጆቻችን የሠሯቸውን፣ ‘አምላኮቻችን’ አንላቸውም፤ ድኻ አደጉ ከአንተ ርኅራኄ ያገኛልና።”