ዘኍል 24:11 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በል ቶሎ ወደ ቤትህ ሂድልኝ፤ ወሮታህን አሳምሬ ልከፍልህ ነበር፤ እግዚአብሔር ግን እንዳታገኝ ከለከለህ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንግዲህ አሁን ወደ ስፍራህ ሽሽ፤ እኔም እንዲህ አልሁ፦ ‘በእውነት አከብርህ ዘንድ ወድጄ ነበር፤’ ጌታ ግን፥ እነሆ፥ ክብርህን ከለከለህ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንግዲህስ በቶሎ ወደ ቤትህ ሂድ! እኔ በርግጥ ብዙ ዋጋ ልከፍልህ ቃል ገብቼልህ ነበር፤ ነገር ግን ይህን ዋጋ እንዳታገኝ እግዚአብሔር ዘግቶብሃል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆም፥ ፈጽመህ መረቅሃቸው፤ ይህ ሦስተኛህ ነው፤ አሁንም እንግዲህ ወደ ስፍራህ ሂድ፤ እኔ አከብርሃለሁ ብዬ ነበር፤ እግዚአብሔር ግን እነሆ፥ ክብርህን ከለከለ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔ አከብርህ ዘንድ ወድጄ ነበር፤ እግዚአብሔር ግን፥ እነሆ፥ ክብርህን ከለከለ አለው። |
ከዚያም ባላቅ፣ በበለዓም ላይ እጅግ ተቈጣ፤ እጆቹንም አጨብጭቦ እንዲህ አለው፤ “ጠላቶቼን እንድትረግምልኝ ጠራሁህ፤ አንተ ግን ሦስቱንም ጊዜ ባረክሃቸው።
ከዚህም በላይ ለርሱ ብዬ ሁሉን ነገር የተውሁለትን፣ ወደር የሌለውን ጌታዬን ክርስቶስ ኢየሱስን ከማወቅ ታላቅነት ጋራ ሳነጻጽር፣ ሁሉንም ነገር እንደ ጕድለት እቈጥረዋለሁ፤ ለርሱ ስል ሁሉን ዐጥቻለሁ፤ ክርስቶስን አገኝ ዘንድ ሁሉን እንደ ጕድፍ እቈጥራለሁ፤