ዘኍል 22:31 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ጊዜ እግዚአብሔር የበለዓምን ዐይን ከፈተ፤ እርሱም የእግዚአብሔር መልአክ የተመዘዘ ሰይፍ እንደ ያዘ መንገዱ ላይ ቆሞ አየ፤ ጐንበስ ብሎም በግንባሩ ተደፋ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም የበለዓምን ዐይኖች ከፈተ፤ የጌታም መልአክ በመንገድ ላይ ቆሞ የተምዘዘም ሰይፍ በእጁ ይዞ አየ፤ ሰገደም፥ በግምባሩም ወደ መሬት ተደፋ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር በለዓም ሰይፍ ይዞ የቆመውን መልአክ ለማየት እንዲችል አደረገው፤ በለዓምም በግንባሩ ወደ መሬት ተደፋ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም የበለዓምን ዐይኖች ከፈተ፤ የእግዚአብሔርንም መልአክ በመንገድ ላይ ቆሞ፥ የተመዘዘም ሰይፍ በእጁ ይዞ አየ፤ በግንባሩም ወድቆ ሰገደለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም የበለዓምን ዓይኖች ከፈተ፤ የእግዚአብሔርም መልአክ በመንገድ ላይ ቆሞ የተምዘዘም ሰይፍ በእጁ ይዞ አየ፤ ሰገደም፥ በግምባሩም ወደቀ። |
ዳዊት ቀና ብሎ ሲመለከት፣ የእግዚአብሔር መልአክ በሰማይና በምድር መካከል ቆሞ አየ፤ መልአኩም በኢየሩሳሌም ላይ የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ ይዞ ነበር፤ ከዚያም ዳዊትና ሽማግሌዎቹ ማቅ እንደ ለበሱ በግምባራቸው ተደፉ።
አህያዪቱም ደግሞ በለዓምን እንዲህ አለችው፣ “ከብዙ ጊዜ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ የተቀመጥህብኝ አህያህ አይደለሁምን? ታዲያ ይህን የመሰለ ነገር የማድረግ ልማድ ነበረኝ?” እርሱም፣ “በጭራሽ!” አላት።
የዚያ የአምላክን ቃል የሚሰማ፣ ከልዑልም ዕውቀትን ያገኘው፣ ከሁሉን ቻይ ራእይ የሚገለጥለት፣ መሬት የተደፋው፣ ዐይኖቹም የተገለጡለት ሰው ንግር፤
አንተም ዐይናቸውን ትከፍታለህ፤ ከጨለማ ወደ ብርሃን፣ ከሰይጣንም ሥልጣን ወደ እግዚአብሔር ትመልሳቸዋለህ፤ እነርሱም የኀጢአትን ይቅርታ ይቀበላሉ፤ በእኔም በማመን በተቀደሱት መካከል ርስት ያገኛሉ።’
ኢያሱ በኢያሪኮ አጠገብ ሳለ፣ ቀና ብሎ ሲመለከት የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ የያዘ አንድ ሰው ከፊቱ ቆሞ አየ። ኢያሱም ወደ እርሱ ቀርቦ፤ “ከእኛ ወገን ነህ ወይስ ከጠላቶቻችን?” ሲል ጠየቀው።
እርሱም፣ “አይደለሁም፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር ሰራዊት አለቃ በመሆኔ እነሆ፤ መጥቻለሁ” ሲል መለሰለት፤ ኢያሱም በግንባሩ ተደፍቶ ሰገደና፣ “ጌታዬ ለባሪያው የሚነግረው ምንድን ነው?” አለው።