ወደ እግዚአብሔር በጮኽን ጊዜ ግን ጩኸታችንን ሰማ፤ መልአክ ልኮም ከግብጽ አወጣን። “አሁንም ያለነው እዚሁ ቃዴስ በግዛትህ ድንበር ላይ ባለችው ከተማ ነው።
ዘኍል 21:22 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አገርህን አቋርጠን እንድናልፍ ፍቀድልን፤ ወደ የትኛውም ዕርሻ ሆነ የወይን አትክልት አንገባም፤ ወይም ከየትኛውም ጕድጓድ ውሃ አንጠጣም። ከግዛትህ እስክንወጣ ድረስም የንጉሡን አውራ ጐዳና አንለቅም።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “በምድርህ ላይ ልለፍ፤ ወደ እርሻና ወደ ወይን ቦታ አንገባም፤ ከጉድጓድም ውኃን አንጠጣም፤ ግዛትህን አልፈን እስክንወጣ ድረስ በንጉሥ ጐዳና እንሄዳለን።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በምድርህ አልፈን እንድንሄድ ፍቀድልን፤ እኛና ከብቶቻችን ከመንገዱ አንወጣም፤ ወደ እርሻዎችህም ሆነ ወደ ወይን ተክሎችህ አንገባም፤ ከውሃ ጒድጓዶችህም ውሃ አንጠጣም፤ ከግዛትህ እስክንወጣ ድረስ ዋናውን መንገድ አንለቅም።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በምድርህ ላይ እንለፍ፤ በመንገዱም እንሄዳለን፤ ወደ እርሻና ወደ ወይን ቦታ አንገባም፤ ከጕድጓድህም ውኃን አንጠጣም፤ እስክንወጣ ድረስ በንጉሥ ጎዳና እንሄዳለን።” |
ወደ እግዚአብሔር በጮኽን ጊዜ ግን ጩኸታችንን ሰማ፤ መልአክ ልኮም ከግብጽ አወጣን። “አሁንም ያለነው እዚሁ ቃዴስ በግዛትህ ድንበር ላይ ባለችው ከተማ ነው።
ስለዚህ በአገርህ እንድናልፍ እባክህን ፍቀድልን፤ በየትኛውም ዕርሻ ወይም የወይን ተክል ውስጥ አንገባም፤ ከየትኛውም ጕድጓድ ውሃ አንጠጣም። የንጉሡን አውራ ጐዳና ይዘን ከመጓዝ በቀር፣ ግዛትህን ዐልፈን እስክንሄድ ድረስ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አንልም።”