ዘኍል 17:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ለእስራኤላውያን ንገራቸውና ከየነገዱ አለቆች አንዳንድ፣ በአጠቃላይ ዐሥራ ሁለት በትር ተቀበል፤ የያንዳንዱንም ሰው ስም በየበትሩ ላይ ጻፈው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ለእስራኤል ልጆች ተናገር፥ ከእነርሱም ከእያንዳንዱ ከየአባቶቻቸው ቤት አንድ አንድ በትር፥ ከአለቆቻቸው ሁሉ ከየአባቶቻቸው ቤት ዐሥራ ሁለት በትሮች፥ ውሰድ፤ የእያንዳንዱንም ስም በየበትሩ ላይ ጻፍ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የእስራኤል ሕዝብ ከያንዳንዱ የነገድ መሪ አንዳንድ በትር ተቀብለው ዐሥራ ሁለት በትሮች እንዲሰጡህ ጠይቃቸው፤ የእያንዳንዱንም ስም በበትሩ ላይ ጻፍ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ለእስራኤል ልጆች ንገራቸው፤ ከእነርሱም ከእያንዳንዱ ከየአባቶቻቸው ቤት አንድ አንድ በትር፥ ከአለቆቻቸውም ከየአባቶቻቸው ቤት ዐሥራ ሁለት በትሮች ውሰድ፤ የእያንዳንዱንም ስም በየበትሩ ላይ ጻፍ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለእስራኤል ልጆች ንገራቸው፥ ከእነርሱም ከእያንዳንዱ ከየአባቶቻቸው ቤት አንድ አንድ በትር፥ ከአለቆቻቸው ከየአባቶቻቸው ቤት አሥራ ሁለት በትሮች፥ ውሰድ፤ የእያንዳንዱንም ስም በየበትሩ ላይ ጻፍ። |
በትውልድ መዝገብ በየቤተ ሰባቸው ተቈጥረው ለገቡት ካህናት፣ ዕድሜያቸው ሃያ ዓመትና ከዚያም በላይ ለሆናቸው ሌዋውያን እንደየኀላፊነታቸው መጠንና እንደየምድብ ሥራቸው አካፈሏቸው።
ከዋና ቅርንጫፎቿ ከአንዱ እሳት ወጣ፤ ፍሬዋንም በላ። በትረ መንግሥት የሚሆን፣ አንድም ጠንካራ ቅርንጫፍ አልተረፈም።’ ይህ ሙሾ ነው፤ ለሐዘን እንጕርጕሮም ይሆናል።”
የተሳለው ሊገድል፣ የተወለወለውም እንደ መብረቅ ሊብረቀረቅ ነው! “ ‘ታዲያ፣ እንዴት ደስ ሊለን ይችላል? ሰይፉ የልጄን በትረ መንግሥት እንደ ማንኛውም በትር ንቋል።
ብቻቸውን በዱር ውስጥ፣ በለመለመ መስክ የሚኖሩትን፣ የርስትህ መንጋ የሆኑትን፣ ሕዝብህን በበትርህ ጠብቅ፤ እንደ ቀድሞው ዘመን፣ በባሳንና በገለዓድ ይሰማሩ።
ሙሴ የማደሪያ ድንኳኑን ተክሎ ካበቃ በኋላ ማደሪያ ድንኳኑንና ዕቃዎቹን ሁሉ ቀባቸው፤ ቀደሳቸውም፤ እንደዚሁም መሠዊያውንና ዕቃዎቹን በሙሉ ቀባቸው፤ ቀደሳቸውም።