ዘኍል 11:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ የተነሣም የቦታው ስም፣ “ተቤራ” ተባለ፤ የእግዚአብሔር እሳት በመካከላቸው ነድዳለችና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጌታም እሳት በመካከላቸው ስለ ነደደ የዚያን ስፍራ ስም ተቤራ ብሎ ጠራው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእግዚአብሔር እሳት በዚያ ስፍራ በመካከላቸው ስለ ነደደ ያ ስፍራ “ታብዔራ” ተብሎ ተጠራ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእግዚአብሔርም ዘንድ በእነርሱ ላይ እሳት ስለ ነደደች የዚያ ስፍራ ስም “መካነ ውዕየት” ተብሎ ተጠራ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔርም እሳት በመካከላቸው ስለነደደች የዚያን ስፍራ ስም ተቤራ ብሎ ጠራው። |