ዘኍል 11:19 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የምትበሉትም ለአንድ ወይም ለሁለት ቀን ወይም ለዐምስት፣ ለዐሥር ወይም ለሃያ ቀን አይደለም፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንድ ቀን ወይም ሁለት ቀን ወይም አምስት ቀን ወይም ዐሥር ቀን ወይም ሀያ ቀን ብቻ የምትበሉት አይደለም፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የምትበሉትም ለአንድ ወይም ለሁለት ቀን ለአምስት፥ ለዐሥር ወይም ለኻያ ቀን ብቻ አይደለም፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንድ ቀን፥ ወይም ሁለት ቀን፥ ወይም አምስት ቀን፥ ወይም ዐሥር ቀን ወይም ሃያ ቀን አትበሉም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንድ ቀን ወይም ሁለት ቀን ወይም አምስት ቀን ወይም አሥር ቀን ወይም ሀያ ቀን አትበሉም፤ |
“ለሕዝቡ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፤ ‘ነገ ሥጋ ትበላላችሁና ራሳችሁን በመቀደስ ተዘጋጁ። “በግብጽ ተመችቶን ነበር፤ አሁን ግን ሥጋ ማን ይሰጠናል!” ብላችሁ ያለቀሳችሁትን እግዚአብሔር ሰምቷል፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ሥጋ ይሰጣችኋል፤ እናንተም ትበላላችሁ።
ነገር ግን በአፍንጫችሁ እስኪወጣና እስኪያንገፈግፋችሁ ድረስ ወር ሙሉ ትበሉታላችሁ፤ በመካከላችሁ ያለውን እግዚአብሔርን ንቃችሁ በፊቱ፣ “ለምን ከግብጽ ወጣን?” ብላችሁ አልቅሳችኋልና።’ ”