ዘኍል 1:17 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴና አሮን ስማቸው የተጠቀሰውን እነዚህን ሰዎች ወሰዱ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴና አሮንም እነዚህን በስማቸው ተጠርተው የነበሩትን ሰዎች ወሰዱአቸው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሙሴና አሮን እነዚህን ስሞቻቸው የተጠቀሱትን ሰዎች ወሰዱ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴና አሮንም እነዚህን በየስማቸው የተጠሩትን ሰዎች ወሰዱአቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴና አሮንም እነዚህን በስማቸው የተጠሩትን ሰዎች ወሰዱአቸው፤ |
ከዚያም በሁለተኛው ወር በመጀመሪያው ቀን ማኅበረ ሰቡን በሙሉ በአንድነት ሰበሰቧቸው። የተሰበሰቡትም በየጐሣቸውና በየቤተ ሰባቸው የትውልድ ሐረጋቸውን ተናገሩ፤