La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ነህምያ 7:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከተማዪቱ ታላቅና ሰፊ ነበረች፤ የሚኖርባት ሕዝብ ግን ጥቂት ሲሆን፣ ቤቶች ገና አልተሠሩባትም ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከተማይቱ ሰፊና ታላቅ ነበረች፤ በውስጧ የነበሩ ሕዝብ ግን ጥቂቶች ነበሩ፤ ቤቶችም አልተሠሩም ነበር።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ኢየሩሳሌም ታላቅና ሰፊ ከተማ ሆና ነበር፤ ነገር ግን የሚኖርባት ሕዝብ ቊጥር አነስተኛ ነበር፤ ገና ብዙ ቤቶችም አልተሠሩባትም፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ከተ​ማ​ዪ​ቱም ሰፊና ታላቅ ነበ​ረች፤ በው​ስ​ጥዋ የነ​በሩ ሕዝብ ግን ጥቂ​ቶች ነበሩ፤ ቤቶ​ቹም ገና አል​ተ​ሠ​ሩም ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ከተማይቱም ሰፊና ታላቅ ነበረች፥ በውስጥዋ የነበሩ ሕዝብ ግን ጥቂቶች ነበሩ፥ ቤቶቹም አልተሠሩም ነበር።

Ver Capítulo



ነህምያ 7:4
7 Referencias Cruzadas  

በዚህ ጊዜ የሕዝቡ መሪዎች መኖሪያቸውን በኢየሩሳሌም አደረጉ፤ ከቀረው ሕዝብ ከዐሥር አንዱ እጅ በቅድስቲቱ ከተማ በኢየሩሳሌም፣ የቀሩት ዘጠኙ እጅ ደግሞ በየራሳቸው ከተሞች እንዲኖሩ ዕጣ ተጣጣሉ።


ሕዝቡም በኢየሩሳሌም ለመኖር በራሳቸው ፈቃድ የተነሣሡትን ሰዎች ሁሉ አመሰገኑ።


ለእነርሱም፣ “የኢየሩሳሌም በሮች ፀሓይ ሞቅ እስክትል ድረስ አይከፈቱም፤ በር ጠባቂዎቹ ዘብ በሚቆሙበት ጊዜ ሁሉ፣ በሮቹን ይዝጓቸው፤ መወርወሪያም ያድርጉባቸው፣ እንዲሁም ከኢየሩሳሌም ነዋሪዎች አንዳንዶቹን በየጥበቃ ቦታቸው፣ አንዳንዶቹን ደግሞ በየቤታቸው አጠገብ እንዲቆሙ መድቡ” አልኋቸው።


ስለዚህ መኳንንቱን፣ ሹማምቱንና ተራውን ሕዝብ ሰብስቤ በየቤተ ሰቡ ይመዘገቡ ዘንድ እግዚአብሔር ይህን በልቤ አኖረ። ወደ ምድራቸው ለመመለስ የመጀመሪያ የሆኑትን ሰዎች የትውልድ ሐረግ መዝገብ አገኘሁ፤ ተጽፎ ያገኘሁትም ይህ ነው።


ወገኖችህ የቀድሞ ፍርስራሾችን መልሰው ይሠራሉ፤ የጥንቱንም መሠረት ያቆማሉ፤ አንተም፣ የተናዱ ቅጥሮችን ዐዳሽ፣ ባለአውራ መንገድ ከተሞችን ጠጋኝ ትባላለህ።


ከሁሉ አስቀድማችሁ ግን የእግዚአብሔርን መንግሥትና ጽድቁን ፈልጉ፤ እነዚህም ሁሉ ይጨመሩላችኋል።