ነህምያ 3:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሮጌውን በር የፋሴሐ ልጅ ዮዳሄና የበሶድያ ልጅ ሜሱላም መልሰው ሠሩ፤ እነርሱም ምሰሶዎቹን አቁመው መዝጊያዎቹን፣ ማያያዣዎቹንና መወርወሪያዎቹን በየቦታቸው አኖሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የፋሴሐ ልጅ ዮያዳ የቤሶዴያ ልጅ ሜሹላም “አሮጌ በር” አደሱ፤ ሰረገሎቹን አኖሩ፥ በሮቹንም አቆሙ፥ ቁልፎቹንና መወርወሪያዎቹንም አደረጉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የፓሴሕ ልጅ ዮዳሄ፥ የበሶድያ ልጅ መሹላም የይሻናን ቅጽር በር ሠሩ፤ ምሰሶዎችንም አቆሙለት፤ በሮችንም ገጠሙ፤ ለበሮቹም ቊልፎችንና መወርወሪያዎችን አበጁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የፋሴሓ ልጅ ኢዮዳሄና የበሶድያ ልጅ ሜሱላም አሮጌውን በር አደሱ፤ ሰረገሎቹን አኖሩ፤ ሳንቃዎቹንም አቆሙ፤ ቍልፎቹንና መወርወሪያዎቹንም አደረጉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የፋሴሐ ልጅ ዮዳሄና የበሶድያ ልጅ ሜሱላም አሮጌውን በር አደሱ፥ ሰረገሎቹን አኖሩ፥ ሳንቃዎቹንም አቆሙ፥ ቁልፎቹንና መወርወሪያዎቹንም አደረጉ። |
ከዚያም ከኤፍሬም በር በላይ፣ በአሮጌ በር፣ በዓሣ በር፣ በሐናንኤል ግንብ፣ በመቶዎቹ ግንብ ዐልፌ እስከ በጎች በር ድረስ ተከተልኋቸው። እነርሱም በዘበኞች በር አጠገብ ሲደርሱ ቆሙ።