ስለዚህም ኢዮአብ ወደ ቴቁሔ፤ ሰው ልኮ አንዲት ብልኅ የሆነች ሴት አስመጣ፤ እንዲህም አላት፤ “ሐዘንተኛ በመምሰል የሐዘን ልብስ ልበሺ፤ ዘይት አትቀቢ፤ ለሞተ ሰው ብዙ ጊዜ እንዳዘነች ሴት መስለሽም ታዪ።
ነህምያ 3:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሚቀጥለውን ክፍል የቴቁሔ ሰዎች መልሰው ሠሩ፤ መኳንንታቸው ግን በተቈጣጣሪ አሠሪዎቻቸው ሥር ሆነው በሥራው መጠመድ አልፈለጉም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአጠገባቸውም ቴቁአውያን አደሱ፤ መኳንንቶቻቸው ግን ለጌታቸው ሥራ አንገታቸውን አልሰጡም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የተቆዓ ከተማ ሰዎች ከዚያ ቀጥሎ ያለውን ክፍል ሠሩ፤ ነገር ግን የከተማይቱ ሹማምንት በተቈጣጣሪዎች የተመደበላቸውን የጒልበት ሥራ መሥራትን እምቢ አሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአጠገባቸውም ቴቁሓውያን ይሠሩ ጀመሩ፤ ታላላቆቻቸው ግን ለሥራው አንገታቸውን አላዋረዱም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአጠገባቸውም ቴቁሐውያን አደሱ፥ ታላላቆቻቸው ግን ለጌታቸው ሥራ አንገታቸውን አላዋረዱም። |
ስለዚህም ኢዮአብ ወደ ቴቁሔ፤ ሰው ልኮ አንዲት ብልኅ የሆነች ሴት አስመጣ፤ እንዲህም አላት፤ “ሐዘንተኛ በመምሰል የሐዘን ልብስ ልበሺ፤ ዘይት አትቀቢ፤ ለሞተ ሰው ብዙ ጊዜ እንዳዘነች ሴት መስለሽም ታዪ።
የአቆስ ልጅ የኦርዮ ልጅ ሜሪሞት ከዚያ ቀጥሎ ያለውን ክፍል መልሶ ሠራ። ከርሱ ቀጥሎ ያለውን የሜሴዜቤል ልጅ የቤራክያ ልጅ ሜሱላም መልሶ ሠራ። ከርሱ ቀጥሎ ያለውን የበዓና ልጅ ሳዶቅ መልሶ ሠራ፤
አሮጌውን በር የፋሴሐ ልጅ ዮዳሄና የበሶድያ ልጅ ሜሱላም መልሰው ሠሩ፤ እነርሱም ምሰሶዎቹን አቁመው መዝጊያዎቹን፣ ማያያዣዎቹንና መወርወሪያዎቹን በየቦታቸው አኖሩ።
ለይሁዳ ንጉሥ ለሴዴቅያስም ይህንኑ መልእክት እንዲህ ብዬ ነገርሁት፤ “ዐንገታችሁን ከባቢሎን ንጉሥ ቀንበር በታች ዝቅ አድርጉ፤ እርሱንና ሕዝቡን አገልግሉ፤ በሕይወትም ትኖራላችሁ።
“ ‘ “ነገር ግን ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆር የማይገዛ፣ ዐንገቱንም ከቀንበሩ በታች ዝቅ የማያደርግ ማንኛውንም ሕዝብ ወይም መንግሥት በእጁ እስከማጠፋው ድረስ በሰይፍና በራብ፣ በመቅሠፍትም እቀጣዋለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር፤
“እናንተ የብንያም ልጆች፤ ክፉ ነገር፣ ታላቅም ጥፋት ከሰሜን ድንገት ይመጣልና፣ ከኢየሩሳሌም ሸሽታችሁ አምልጡ፤ በቴቁሔ መለከትን ንፉ፤ በቤትሐካሪም ላይ ምልክት ከፍ አድርጋችሁ አሳዩ።
በቴቁሔ ከነበሩት እረኞች መካከል አንዱ የሆነው አሞጽ፣ ዖዝያን የይሁዳ ንጉሥ በነበረ ጊዜ እንዲሁም የዮአስ ልጅ ኢዮርብዓም የእስራኤል ንጉሥ በነበረ ጊዜ፣ ይኸውም የምድር መናወጥ ከመሆኑ ከሁለት ዓመት በፊት ስለ እስራኤል ያየውና የተናገረው ቃል ይህ ነው፤
እንግዲህ፣ አባቶቻችንም እኛም ልንሸከመው ያልቻልነውን ቀንበር በደቀ መዛሙርት ጫንቃ ላይ በመጫን ለምን አሁን እግዚአብሔርን ትፈታተኑታላችሁ?
ወንድሞች ሆይ፤ በተጠራችሁ ጊዜ ምን እንደ ነበራችሁ እስኪ አስቡ። በሰው መስፈርት ከእናንተ ብዙዎቻችሁ ዐዋቂዎች አልነበራችሁም፤ ብዙዎቻችሁም ኀያላን አልነበራችሁም፤ ብዙዎቻችሁም ከትልቅ ቤተ ሰብ አልተወለዳችሁም።
የእግዚአብሔር መልአክ፣ ‘ሜሮዝን ርገሙ፤’ ‘ሕዝቧንም ዐብራችሁ ርገሙ፤ ከኀያላን ሰልፍ እግዚአብሔርን ለመርዳት፣ በእግዚአብሔርም ጐን ለመቆም አልመጡምና’ አለ።