ሚክያስ 1:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ተራሮች ከሥሩ ይቀልጣሉ፤ ሸለቆዎችም ይሰነጠቃሉ፤ በእሳት ፊት እንዳለ ሰም፣ በገደል ላይ እንደሚወርድ ፈሳሽ ይሆናሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ተራሮች በሥሩ ይቀልጣሉ፥ ሸለቆዎችም በእሳት ፊት እንዳለ ሰም፥ ከቁልቁለት እንደሚወርድ ውኃ፥ ይሰነጠቃሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ጊዜ ሰም በእሳት እንደሚቀልጥና፥ ውሃም ከከፍተኛ ቦታ ወደ ታች እንደሚወርድ እንዲሁም ተራራዎች ከእርሱ ሥር ይቀልጣሉ፤ ሸለቆዎችም ይከፈታሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ተራሮችም በእሳት ፊት እንዳለ ሰም፥ በገደልም ወርዶ እንደሚፈስስ ውኃ፥ በበታቹ ይቀልጣሉ፥ ሸለቆችም ይሰነጠቃሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ተራሮችም በእሳት ፊት እንዳለ ሰም፥ በገደልም ወርዶ እንደሚፈስስ ውኃ፥ በበታቹ ይቀልጣሉ፥ ሸለቆችም ይሰነጠቃሉ። |
ጌታ እግዚአብሔር፣ የሰራዊት ጌታ፣ ምድርን ይዳስሳል፤ እርሷም ትቀልጣለች፤ በውስጧ የሚኖሩ ሁሉ ያለቅሳሉ፤ የምድር ሁለመና እንደ አባይ ወንዝ ይነሣል፤ እንደ ግብጽ ወንዝም ይወርዳል።
ቆመ፤ ምድርን አንቀጠቀጠ፤ ተመለከተ፤ ሕዝቦችን አብረከረከ፤ የዘላለም ተራሮች ተፈረካከሱ፤ የጥንት ኰረብቶችም ፈራረሱ፤ መንገዱ ዘላለማዊ ነው።
በዚያ ቀን እግሮቹ ከኢየሩሳሌም በስተምሥራቅ በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ይቆማሉ፤ የደብረ ዘይት ተራራም ታላቅ ሸለቆን በመሥራት የተራራውን እኩሌታ ወደ ሰሜን፣ እኩሌታውንም ወደ ደቡብ በማድረግ ምሥራቅና ምዕራብ ሆኖ ለሁለት ይከፈላል፤
“እግዚአብሔር ሆይ፤ ከሴይር በወጣህ ጊዜ፣ ከኤዶም ምድርም በተነሣህ ጊዜ፣ ምድር ተንቀጠቀጠች፤ ሰማያትም ዝናብ አዘነቡ፤ ደመናዎችም ውሃ አፈሰሱ።