Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 68:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ጢስ እንደሚበንን፣ እንዲሁ አብንናቸው። ሰም በእሳት ፊት እንደሚቀልጥ፣ ክፉዎችም እንዲሁ ከእግዚአብሔር ፊት ይጥፉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 እግዚአብሔር ይነሣ፥ ጠላቶቹም ይበተኑ፥ የሚጠሉትም ከፊቱ ይሽሹ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ጢስ በነፋስ በኖ እንደሚጠፋ አብንናቸው፤ ሰም በእሳት ቀልጦ እንደሚያልቅ ክፉዎችም ከእግዚአብሔር ፊት ይጥፉ!

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 በጥ​ልቅ ረግ​ረግ ጠለ​ቅሁ ኀይ​ልም የለ​ኝም፤ ወደ ጥልቁ ባሕ​ርም ደረ​ስሁ ማዕ​በ​ሉም አሰ​ጠ​መኝ።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 68:2
17 Referencias Cruzadas  

ተራሮች ከሥሩ ይቀልጣሉ፤ ሸለቆዎችም ይሰነጠቃሉ፤ በእሳት ፊት እንዳለ ሰም፣ በገደል ላይ እንደሚወርድ ፈሳሽ ይሆናሉ።


ክፉዎች ግን ይጠፋሉ፤ የእግዚአብሔር ጠላቶች እንደ መስክ ውበት ይሆናሉ፤ ይጠፋሉ፤ እንደ ጢስም ተነው ይጠፋሉ።


ስለዚህ እንደ ማለዳ ጉም፣ ፈጥኖ እንደሚጠፋ የጧት ጤዛ፣ ከዐውድማ እንደሚጠረግ እብቅ፣ በመስኮትም እንደሚወጣ ጢስ ይሆናሉ።


እንግዲህ ርኩሰት እንደ እሳት ይቀጣጠላል፤ እሾኽንና ኵርንችትን ይበላል፤ ጥቅጥቅ ያለውን ደን ያነድዳል፤ ጢሱም ተትጐልጕሎ እንደ ዐምድ ይቆማል።


ተራሮች በእግዚአብሔር ፊት፣ በምድርም ሁሉ ጌታ ፊት እንደ ሰም ቀለጡ።


እርሷም በእሳት ተቃጥላለች፤ የግንባርህ ተግሣጽ ያጠፋቸዋል።


እሳት ሲለኰስ ጭራሮን እንደሚያቀጣጥል፣ ውሃንም እንደሚያፈላ፣ ስምህ በጠላቶችህ ዘንድ እንዲታወቅ ውረድ፤ መንግሥታትም በፊትህ እንዲንቀጠቀጡ አድርግ!


መፈራት ያለብህ አንተ ብቻ ነህ፤ በተቈጣህ ጊዜ ማን በፊትህ መቆም ይችላል?


እንደ ውሃ ፈሰስሁ፤ ዐጥንቶቼም ሁሉ ከመጋጠሚያቸው ወለቁ፤ ልቤ እንደ ሰም ሆነ፤ በውስጤም ቀለጠ።


ታቦቱ ለጕዞ በተነሣ ጊዜ ሁሉ ሙሴ፣ “እግዚአብሔር ሆይ፤ ተነሥ! ጠላቶችህ ይበተኑ፤ የሚጠሉህም ከፊትህ ይሽሹ” ይል ነበር።


ከዚያም ኢዮአብና ዐብሮት የነበረው ሰራዊት ሶርያውያንን ለመውጋት ወደ ፊት ገሠገሠ፤ ሶርያውያንም ከፊቱ ሸሹ።


ሶርያውያንም ለጦርነት ተሰልፈው ዳዊትን በግንባር ገጠሙት፤ ይሁን እንጂ ከእስራኤል ፊት ሸሹ፤ ዳዊትም ሰባት መቶ ሠረገለኞችንና አርባ ሺሕ እግረኛ ወታደሮች ገደለባቸው። እንዲሁም የሰራዊታቸውን አዛዥ ሶባክን አቍስሎት ስለ ነበር፣ እዚያው ሞተ።


ሕዝቦች በድምፅህ ነጐድጓድ ይሸሻሉ፤ መንግሥታት ስትነሣ ይበተናሉ።


ጦረኞችህ ለምን ተዘረሩ? እግዚአብሔር ገፍትሮ ስለሚጥላቸው መቆም አይችሉም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios