ማቴዎስ 9:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን የሰው ልጅ በምድር ላይ ኀጢአትን የማስተስረይ ሥልጣን እንዳለው እንድታውቁ ነው” ብሎ፣ ሽባውን፣ “ተነሣ! ቃሬዛህን ይዘህ ወደ ቤትህ ሂድ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን በምድር ላይ ኃጢአቶችን ሊያስተሰርይ የሰው ልጅ ሥልጣን እንዳለው እንድታውቁ ነው፤” በዚያን ጊዜ ሽባውን “ተነሣ፤ አልጋህን ተሸከምና ወደ ቤትህ ሂድ፤” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን የሰው ልጅ በምድር ላይ ኃጢአትን ለማስተስረይ ሥልጣን እንዳለው ታውቁ ዘንድ” ሽባውን ሰው “ተነሥና አልጋህን ተሸክመህ ወደ ቤትህ ሂድ” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን በምድር ላይ ኀጢአትን ያስተሰርይ ዘንድ ለሰው ልጅ ሥልጣን እንዳለው እንድታውቁ፤” በዚያን ጊዜ ሽባውን “ተነሣ፤ አልጋህን ተሸከምና ወደ ቤትህ ሂድ፤” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን በምድር ላይ ኃጢአትን ያስተሰርይ ዘንድ ለሰው ልጅ ሥልጣን እንዳለው እንድታውቁ፥ በዚያን ጊዜ ሽባውን፦ ተነሣ፤ አልጋህን ተሸከምና ወደ ቤትህ ሂድ አለው። |
የርስቱን ትሩፍ ኀጢአት ይቅር የሚል፣ የሚምር እንደ አንተ ያለ አምላክ ማነው? ለዘላለም አትቈጣም፤ ነገር ግን ምሕረት በማድረግ ደስ ይልሃል።
ከዚህም የተነሣ ዝናው በመላዋ ሶርያ ተሰማ፤ ሕዝቡም በተለያዩ በሽታዎች የታመሙትን፣ በክፉ ደዌ የሚሠቃዩትን፣ አጋንንት ያደሩባቸውን፣ የሚጥል በሽታ ያለባቸውን፣ ሽባዎችን ሁሉ ወደ እርሱ አመጡ፤ ፈወሳቸውም።
በዚያም ሰዎች አንድ ሽባ ሰው በቃሬዛ ተሸክመው ወደ እርሱ አመጡ። ኢየሱስም እምነታቸውን አይቶ ሽባውን፣ “አይዞህ አንተ ልጅ፤ ኀጢአትህ ተሰርዮልሃል” አለው።
“ይህ ሰው እንዴት እንዲህ ይላል? በአምላክ ላይ የስድብ ቃል እየተናገረ እኮ ነው! ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ኀጢአትን ሊያስተሰርይ ማን ይችላል?” ብለው አሰቡ።
ጸሐፍትና ፈሪሳውያንም፣ “አምላክን በመሳደብ እንዲህ የሚናገር ይህ ማን ነው? ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ኀጢአትን ሊያስተሰርይ ማን ይችላል?” ብለው ያስቡ ጀመር።
እናንተ ይቅር የምትሉትን ሰው እኔም ይቅር እለዋለሁ፤ በርግጥ ይቅር የምለው ነገር ካለ፣ በክርስቶስ ፊት ይቅር የምለው ስለ እናንተ ስል ነው።
ስለዚህ እኛ የክርስቶስ እንደራሴዎች ነን፤ እግዚአብሔርም በእኛ አማካይነት ጥሪውን ያቀርባል፤ እኛም ከእግዚአብሔር ጋራ ታረቁ ብለን በክርስቶስ እንለምናችኋለን።
እርስ በርሳችሁም ተቻቻሉ፤ ከእናንተ አንዱ በሌላው ላይ ቅር የተሠኘበት ነገር ቢኖር ይቅር ተባባሉ፤ ጌታ ይቅር እንዳላችሁ እናንተም ሌላውን ይቅር በሉ።