‘ዘወር በል፤ አትቅረበኝ፤ አትጠጋኝ፤ እኔ ከአንተ ይልቅ ቅዱስ ነኝ!’ የሚሉ ናቸው። እንዲህ ያለው ሕዝብ በአፍንጫዬ ዘንድ እንደ ጢስ፣ ቀኑን ሙሉ እንደሚነድድ እሳት ነው።
ማቴዎስ 9:11 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፈሪሳውያንም ይህን ባዩ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን፣ “መምህራችሁ ከቀረጥ ሰብሳቢዎችና ከኀጢአተኞች ጋራ ለምን ዐብሮ ይበላል?” ብለው ጠየቋቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፈሪሳውያንም ይህንን አይተው ደቀ መዛሙርቱን “መምህራችሁ ከቀራጮችና ከኃጢአተኞች ጋር አብሮ ለምን ይበላል?” አሉአቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፈሪሳውያንም ይህን አይተው ደቀ መዛሙርቱን “መምህራችሁ ከቀራጮችና ከኃጢአተኞች ጋር ስለምን አብሮ ይበላል?” አሉአቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፈሪሳውያንም አይተው ደቀ መዛሙርቱን “መምህራችሁ ከቀራጮችና ከኀጢአተኞች ጋር አብሮ ስለ ምን ይበላል?” አሉአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፈሪሳውያንም አይተው ደቀ መዛሙርቱን፦ መምህራችሁ ከቀራጮችና ከኃጢአተኞች ጋር አብሮ ስለ ምን ይበላል? አሉአቸው። |
‘ዘወር በል፤ አትቅረበኝ፤ አትጠጋኝ፤ እኔ ከአንተ ይልቅ ቅዱስ ነኝ!’ የሚሉ ናቸው። እንዲህ ያለው ሕዝብ በአፍንጫዬ ዘንድ እንደ ጢስ፣ ቀኑን ሙሉ እንደሚነድድ እሳት ነው።
የሰው ልጅ እየበላና እየጠጣ መጣ፤ እነርሱም፣ ‘በልቶ የማይጠግብ፣ ጠጪ እንዲሁም የቀረጥ ሰብሳቢዎችና የኀጢአተኞች ወዳጅ’ አሉት። ጥበብ ትክክለኛ መሆኗ ግን በሥራዋ ተረጋገጠ።”
ኢየሱስ በማቴዎስ ቤት በማእድ ላይ ሳለ፣ ብዙ ቀረጥ ሰብሳቢዎችና ኀጢአተኞች መጥተው ከእርሱና ከደቀ መዛሙርቱ ጋራ ዐብረው ሊመገቡ ተቀመጡ።
የፈሪሳውያን ጸሐፍት ከኀጢአተኞችና ከቀረጥ ሰብሳቢዎች ጋራ ሲበላ ባዩት ጊዜ፣ ደቀ መዛሙርቱን “ከቀረጥ ሰብሳቢዎችና ከኀጢአተኞች ጋራ ለምን ይበላል?” ሲሉ ጠየቋቸው።
ፈሪሳውያንና ጸሐፍታቸውም “ከቀረጥ ሰብሳቢዎችና ‘ከኀጢአተኞች’ ጋራ የምትበሉትና የምትጠጡት ለምንድን ነው?” እያሉ በደቀ መዛሙርቱ ላይ አጕረመረሙ።