ማቴዎስ 8:23 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ኢየሱስ ወደ ጀልባ ገባ፤ ደቀ መዛሙርቱም ተከትለውት ገብተው ሄዱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ጀልባ በገባ ጊዜ ደቀመዛሙርቱ ተከተሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስም ወደ ጀልባ ሲገባ፥ ደቀ መዛሙርቱ ተከተሉት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ታንኳም ሲገባ ደቀ መዛሙርቱ ተከተሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ታንኳም ሲገባ ደቀ መዛሙርቱ ተከተሉት። |
ከዮሐንስ ተልከው የመጡትንም እንዲህ አላቸው፤ “ሄዳችሁ ያያችሁትንና የሰማችሁትን ለዮሐንስ ንገሩት፤ ዐይነ ስውራን ያያሉ፤ ዐንካሶች ይራመዳሉ፤ ለምጻሞች ይነጻሉ፤ ደንቈሮዎች ይሰማሉ፤ ሙታን ይነሣሉ፤ ለድኾችም ወንጌል ይሰበካል፤