“በምድሪቱ ላይ ራብ ወይም ቸነፈር፣ ዋግ ወይም አረማሞ፣ አንበጣ ወይም ኵብኵባ በሚከሠትበት ጊዜ፣ ወይም ከተሞቻቸውን ጠላት በሚከብብበት ጊዜ፣ እንዲሁም ማንኛውም ዐይነት ጥፋት ወይም በሽታ በሚደርስባቸው ጊዜ፣
ማርቆስ 5:29 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሚፈስሰው ደሟም ወዲያውኑ ቆመ፤ ከሥቃይዋ መገላገሏም በሰውነቷ ታወቃት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሚፈሰው ደሟ ወዲያውኑ ቆመ፤ ከሥቃይዋ እንደዳነች በሰውነቷ ታወቃት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሚፈሰው ደምዋም ወዲያውኑ ቆመ፤ ከሕመምዋም እንደ ዳነች በሰውነትዋ ተሰማት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወዲያውም የደምዋ ምንጭ ደረቀ፤ ከሥቃይዋም እንደዳነች በሰውነትዋ አወቀች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወዲያውም የደምዋ ምንጭ ደረቀ ከሥቃይዋም እንደዳነች በሰውነትዋ አወቀች። |
“በምድሪቱ ላይ ራብ ወይም ቸነፈር፣ ዋግ ወይም አረማሞ፣ አንበጣ ወይም ኵብኵባ በሚከሠትበት ጊዜ፣ ወይም ከተሞቻቸውን ጠላት በሚከብብበት ጊዜ፣ እንዲሁም ማንኛውም ዐይነት ጥፋት ወይም በሽታ በሚደርስባቸው ጊዜ፣
እርሱም አለ፤ “የአምላካችሁን እግዚአብሔር ድምፅ በጥንቃቄ ብትሰሙ፣ በፊቱም ትክክል የሆነውን ብትፈጽሙ፣ ትእዛዞቹን ልብ ብትሉና ሥርዐቱንም ሁሉ ብትጠብቁ፣ በግብጻውያን ላይ ያመጣሁባቸውን ማንኛውንም ዐይነት በሽታ በእናንተ ላይ አላመጣም፤ ፈዋሻችሁ እኔ እግዚአብሔር ነኝና።”
“ነገር ግን ቤቱ ከተመረገ በኋላ፣ ካህኑ ሊመረምረው በሚመጣበት ጊዜ ተላላፊው በሽታ ሳይስፋፋ ቢገኝ፣ በሽታው ስለ ለቀቀው ቤቱ ንጹሕ መሆኑን ያስታውቅ።
“ ‘ማንኛውም ሰው በወር አበባዋ ጊዜ ከሴት ጋራ ግብረ ሥጋ ቢፈጽም፣ የፈሳሿን ምንጭ ገልጧልና፣ እርሷም የፈሳሿን ምንጭ ገልጣለችና ሁለቱም ከሕዝባቸው መካከል ተለይተው ይጥፉ።