በዚህ ጊዜ አካዝያስ በሰማርያ ካለው እልፍኝ ሰገነቱ ላይ ሳለ፣ ከዐይነ ርግቡ ሾልኮ ወድቆ ነበርና ታመመ፤ ስለዚህ፣ “ሄዳችሁ ከዚህ ሕመም እድን እንደ ሆነ የአቃሮንን አምላክ ብዔልዜቡልን ጠይቁ” ሲል መልእክተኞች ላከ።
ማርቆስ 3:22 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከኢየሩሳሌም የመጡ ጸሐፍትም፣ “ብዔልዜቡል ዐድሮበታል! አጋንንትን የሚያወጣው በአጋንንት አለቃ ነው” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከኢየሩሳሌም የወረዱ ጸሐፍትም “በብዔልዜቡል ተይዟል! ደግሞም በዚህ በአጋንንት አለቃ አጋንንትን ያወጣል!” ብለው ተናገሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከኢየሩሳሌም የወረዱ የሕግ መምህራን፥ “እርሱ ብዔልዜቡል አለበት! አጋንንትንም የሚያወጣው በዚሁ የአጋንንት አለቃ በሆነው በብዔልዜቡል አማካይነት ነው!” እያሉ አወሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከኢየሩሳሌም የወረዱ ጻፎችም “ብዔል ዜቡል አለበት፤” ደግሞ “በአጋንንት አለቃ አጋንንትን ያወጣል፤” ብለው ተናገሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከኢየሩሳሌም የወረዱ ጻፎችም፦ ብዔል ዜቡል አለበት፤ ደግሞ፦ በአጋንንት አለቃ አጋንንትን ያወጣል ብለው ተናገሩ። |
በዚህ ጊዜ አካዝያስ በሰማርያ ካለው እልፍኝ ሰገነቱ ላይ ሳለ፣ ከዐይነ ርግቡ ሾልኮ ወድቆ ነበርና ታመመ፤ ስለዚህ፣ “ሄዳችሁ ከዚህ ሕመም እድን እንደ ሆነ የአቃሮንን አምላክ ብዔልዜቡልን ጠይቁ” ሲል መልእክተኞች ላከ።
አንድ ቀን ኢየሱስ እያስተማረ ነበር፤ በዚያም ከገሊላና ከይሁዳ መንደሮች ሁሉ እንዲሁም ከኢየሩሳሌም የመጡ ፈሪሳውያንና የሕግ መምህራን ተቀምጠው ነበር፤ ይፈውስም ዘንድ የጌታ ኀይል ከርሱ ጋራ ነበረ።
አይሁድም እንዲህ አሉት፤ “ጋኔን እንዳለብህ አሁን ዐወቅን፤ አብርሃም ሞተ፤ ነቢያትም እንዲሁ፤ አንተ ግን ማንም ቃልህን ቢጠብቅ ሞትን ፈጽሞ እንደማይቀምስ ትናገራለህ።