ማርቆስ 2:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ተቀምጠው የነበሩ አንዳንድ ጸሐፍት ስለዚህ ነገር በልባቸው እያሰላሰሉ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያም ተቀምጠው ከነበሩ አንዳንድ ጻሐፍት በልባቸውም “ይህ ሰው ስለምን እንደዚህ ያለ ስድብ ይናገራል? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያ ተቀምጠው የነበሩ አንዳንድ የሕግ መምህራን በልባቸው እንዲህ አሉ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከጻፎችም አንዳንዶቹ በዚያ ተቀምጠው ነበር በልባቸውም “ይህ ሰው ስለ ምን እንደዚህ ያለ ስድብ ይናገራል? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከጻፎችም አንዳንዶቹ በዚያ ተቀምጠው ነበር በልባቸውም፦ ይህ ሰው ስለ ምን እንደዚህ ያለ ስድብ ይናገራል? |
“ይህ ሰው እንዴት እንዲህ ይላል? በአምላክ ላይ የስድብ ቃል እየተናገረ እኮ ነው! ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ኀጢአትን ሊያስተሰርይ ማን ይችላል?” ብለው አሰቡ።
ኢየሱስም ሐሳባቸውን ዐውቆ እንዲህ አላቸው፤ “እንጀራ ስለሌለን ነው በማለት የምትነጋገሩት ስለ ምንድን ነው? አሁንም አታስተውሉምን? ልብ አትሉምን? ወይስ ልባችሁ ደንድኗል?
በእግዚአብሔር ዕውቀት ላይ በትዕቢት የሚነሣውን ክርክርና ከንቱ ሐሳብ ሁሉ እናፈርሳለን፤ አእምሮንም ሁሉ እየማረክን ለክርስቶስ እንዲታዘዝ እናደርጋለን።