ማርቆስ 16:11 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱ ሕያው መሆኑንና ለርሷም መታየቱን ሲሰሙ አላመኗትም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱ ግን አላመኗትም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርስዋ “ኢየሱስ ከሞት ተነሥቶ፥ በሕይወት አለ፤ እኔም በዐይኔ አይቸዋለሁ፤” ብላ ነገረቻቸው፤ እነርሱ ግን አላመኑአትም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም ሕያው እንደ ሆነ ለእርስዋም እንደ ታያት ሲሰሙ አላመኑም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም ሕያው እንደ ሆነ ለእርስዋም እንደ ታያት ሲሰሙ አላመኑም። |
ኢየሱስም መልሶ፣ “የማታምን ትውልድ ሆይ፤ እስከ መቼ ከእናንተ ጋራ እኖራለሁ? እስከ መቼስ እታገሣችኋለሁ? ልጁን ወደ እኔ አምጡት።” አላቸው።
ሌሎች ደቀ መዛሙርትም፣ “ጌታን አየነው እኮ!” አሉት። እርሱ ግን፣ “በምስማር የተቸነከሩትን የእጆቹን ምልክቶች ካላየሁ፣ ምስማሮቹ በነበሩበት ቦታ ጣቴን ካላደረግሁ፣ በጐኑም እጄን ካላስገባሁ አላምንም” አለ።